አፍሪትራክ አስመጪ ሃላ.የት.የግ ድርጅት የተለያዩ አዲስ የሬኖ መለዋወጫዎች እና የተለያየ መጠን ያላቸው መለዋወጫ ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Other Sale
- Posted Date : 09/01/2021
- Phone Number : 0116294032
- Source : Reporter
- Closing Date : 09/01/2021
Description
የተሸከርካሪ መለዋወጫ እንዲሁም የተለያየ መጠን ያላቸው መለዋወጫ ዕቃዎች ሽያጭ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡– አ.አ.ሃላ.የተ.የግ.ድ/ቁጥ/001/13
ድርጅታችን በ2013/14 በጀት ዓመት የተለያዩ አዲስ የሬኖ መለዋወጫዎች እና የተለያየ መጠን ያላቸው መለዋወጫ ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት ተጫራቾች፡–
- የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ቦሌ ኢምፔርያል በሚገኘው አፍሪትራክ አስመጪ ሃላ.የተ.የግ.ድርጅት ድርጅቱ ዋና መ/ቤት ከፋይናንስ መግዛት ይችላሉ፣
- ተጫራቾች በአካል በመቅረብ የመለዋወጫዎችን ይዘት በመመልከት ከዚህ ደብዳቤ ጋር በአባሪት በቀረበው የዕቃ ዝርዝር ላይ የሚወዳደርበትን ዋጋ ነጠላ ዋጋ (Unit Price) እና ጠቅላላ ዋጋ (Total Price) በግልፅ አሃዞችን በማስቀመጥ ከነቫቱ በመሙላት እስከ መስከረም 27 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 8፡ዐዐ ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎኘ በማሸግ ለዚሁ ጨረታ አገልግልት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የነጠላ ዋጋ የመወዳደሪያ ዋጋ ተደርጎ ይወሰዳል፤በተጫራች የሚቀርብ ዋጋ ማቅረብያ ሰነድ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፤
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤
- ያላሸነፈ ተጫራች ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ውጤቱ እንደተገለፀ ወድያውኑ 1ዐዐ% ገንዘብ ተመላሽ ይደረግለታል፤
- ጨረታው መስከረም 27 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚህ ዕለት ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ ተጫራች በገባው ውል መሰረት በ15 ቀናት ውስጥ ክፍያ ፈጽሞ ንብረቶችን ባያነሳ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፤
- ድርጅቱ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰብያ፦ ጨረታውን ላሸነፈ ተጫራች በውል መሰረት የሪኖ መለዋወጫ እቃዎች ወኪል አከፋፋይ መብትን እንደምንሰጥ በታላቅ ደስታ እንገልጻለን።
ለተጨማሪ ማብራሪያ :-
በስልክ ቁጥር 011 6 29 40 32/33
ፋክስ 011 6 29 40 34
ፖ.ሳ.ቁ. 26065 አዲስ አበባ መጠየቅ ይችላሉ
አድራሻ፡– ቦሌ ኢምፔርያል ጅምናዝየም ፊት ለፊት
አፍሪትራክ አስመጪ ሃላ.የት.የግ ድርጅት