አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ /አ.ማ/ የባለዕዳዎች ንብረት እና አድራሻ ማፈላለግ የአገልግሎት ስራ ግዥ በኮንትራት ለሁለት (2) ዓመት ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

africa-Insurance-done

Overview

 • Category : Labor Supply Service
 • Posted Date : 07/09/2021
 • Phone Number : 0118494427
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 07/28/2021

Description

የንብረት ማፈላለግ  ጨረታ ማስታወቂያ

አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ /አ.ማ/ የባለዕዳዎች ንብረት እና አድራሻ ማፈላለግ የአገልግሎት ስራ ግዥ በኮንትራት ለሁለት (2) ዓመት ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት የጨረታ ሰነዱን ገዝተው የመጫረቻ ሰነዳቸውን ሞልተው ማቅረብ ይችላሉ፡፡

 1. ተጫራቾች ለዚህ ጨረታ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በመጀመሪያ ጋዜጣ ላይ በማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) እየከፈሉ አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ /አ.ማ/ ዋና መ/ቤት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
 2. የጨረታ ሰነዱን ቦሌ ሩዋንዳ አካባቢ ከሚገኘው የኩባንያው ዋና መ/ቤት ገንዘብ ያዥ (ካሸር) ቢሮ ማግኘት ይቻላል፡፡
 3. ተጫራቾች በጨረታ መመሪያው መሰረት የጨረታ ሰነዱን ገፅ 6 እና 7 ብቻ ሞልተው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 4. በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፀውን መመሪያ ያልተከተለ ተጫራች ከውድድር ሊታገድ ይችላል፡፡
 5. እያንዳንዱ የመጫረቻ ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ መቅረብ አለበት፡፡
 6. እያንዳንዱ ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለጸውን የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
 7. ተጫራቾች ሐምሌ 21 ዓ.ም. እስከ ቀኑ 9፡00 (ዘጠኝ) ሰዓት ድረስ የመጫረቻ ሰነዳቸውን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 8. ጨረታው ሐምሌ 21 ዓ.ም. እስከ ከቀኑ 9፡30 (ዘጠኝ ሰዓት ከሰላሳ) ሰዓት ኩባንያው ዋና መስሪያ ቤት አስራ አንደኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
 9. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 10. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 8494427 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

Send me an email when this category has been updated