አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ) የዳይሬክተሮች ቦርድ ዕጩ አባላትን ዝርዝር ለመግለፅ የወጣ ማስታወቂያ

Africa-Insurance-አፍሪካ-ኢንሹራንስ-ኩባንያ-logo

Overview

  • Category : Announcement
  • Posted Date : 11/02/2022
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 11/02/2022

Description

አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ)

AFRICA INSURANCE COMPANY (S.C)

 የዳይሬክተሮች ቦርድ ዕጩ አባላትን ዝርዝር  ለመግለፅ  የወጣ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ተቋማዊ አስተዳደር መመሪያ /Insurance Corporate Governance Directive/ ቁጥር SIB/48/2019 እና በ24ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ባፀደቀው የተሻሻለው የዳሬክተሮች ቦርድ ጥቆማና ምርጫ አፈፃፀም መመሪያ መሠረት የዳሬክተሮች ቦርድ አባላት ጥቆማ ከሰኔ 01/2014 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2014 ዓ.ም መካሄዱ ይታወሳል፡፡

በዚህ መሠረት የዳሬክተሮች ቦርድ የምርጫና ምልመላ ኮሚቴ የቀረቡለትን የጥቆማ መስጫ ፋይሎች ጳጉሜ 01/2014 ዓ.ም በዝርዝር በመመልከት በኢንሹራንስ ኩባንያዎች ተቋማዊ አስተዳደር መመሪያ ቁጥር SIB/48/2019 እና የዳሬክተሮች ቦርድ ጥቆማና ምርጫ አፈፃፀም መመሪያ መሠረት በኮምፒዩተር ሲስተም በመታገዝ የዕጩ ምልመላ አካሂዷል፡፡

በተደረገው ጥቆማ እና ተጨማሪ የመመረጥ ብቃት ማረጋገጫ መሠረት፡-

በሁሉም ባለአክሲዮኖች (በጋራ ጥቆማ) የተጠቆሙት እጩዎች ከአንደኛ እስከ አስራ አራተኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱት ባለአክሲዮኖች ባገኙት ከፍተኛ ድምፅ መሠረት ዕጩ ተወዳዳሪ ሲሆኑ፣ እንዲሁም በተራ ቁጥር አስራ አምስት እና አስራ ስድስት ላይ የተጠቀሱት ባለአክሲዮኖች በተጠባባቂነት ተይዘዋል፣ ተፅእኖ ፈጣሪ ያልሆኑ ባለአክሲዮኖች ብቻ የጠቆሟቸው እጩዎች ከአንደኛ እስከ አራተኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱት ባለአክስዮኖች ባገኙት ከፍተኛ ድምፅ መሠረት ዕጩ ተወዳዳሪ ሆነው ተመዝግበዋል፡፡

ስለሆነም የዳሬክተሮች ቦርድ ጥቆማና ምርጫ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከላይ በተጠቀሱት መመሪያዎች መሠረት የዕጩ የዳሬክተሮች ቦርድ ምልመላ ያካናወነ ሲሆን፣ ኩባንያው በቀጣይ በሚያካሂደው 27ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በሚከናወነው የዳሬክቶች ቦርድ ምርጫ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ መስፈርትን አሟልተው ለዳሬክተሮች ቦርድ አባልነት የቀረቡት ዕጩዎች ከዚህ በታች በየምድባቸው የተዘረዘሩት መሆናቸውን በአክብሮት ያሳውቃል፡፡

ሀ. በሁሉም ባለአክሲዮኖች (በጋራ ጥቆማ) የተጠቆሙ እጩዎች ስም ዝርዝር
ደረጃ የእጩዎች ሙሉ ስም ያገኙት ድምፅ በአክሲዮን ብዛት ምርመራ
1ኛ አቶ ዓለሙ በርሄ ተስፋ 101,035 እጩ የቦርድ አባል
2ኛ ወጋገን ባንክ አ.ማ (በአቶ አክሊሉ ውበት ተወክሎ) 87,203 እጩ የቦርድ አባል
3ኛ አዲስ መለዋወጫ አ.ማ (በአቶ ጌታቸው ታደሰ ተወክሎ) 75,114 እጩ የቦርድ አባል
4ኛ አቶ ብርሃኑ ታደሰ ጎጂ 57,439 እጩ የቦርድ አባል
5ኛ ወ/ሮ እንወይ ገ/መድህን 54,610 እጩ የቦርድ አባል
6ኛ ዮቴክ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማ (በአቶ ኪ/ማሪያም አብረሃ) 39,473 እጩ የቦርድ አባል
7ኛ ንጋት (በወ/ሮ ዓለምፍሬ ደረሰ ተወክሎ) 27,868 እጩ የቦርድ አባል
8ኛ አቶ አብዱራህማን አብዱልባቂ 20,608 እጩ የቦርድ አባል
9ኛ ቱምሣ ኢንዶውመንት (በአቶ ተሾመ ለገሠ ተወክሎ) 19,829 እጩ የቦርድ አባል
10ኛ ወንዶ ኃ/የተ/የግ/ማ (በአቶ ፍቃደስላሴ ቤዛ ተወክሎ) 19,728 እጩ የቦርድ አባል
11ኛ ወ/ሮ ፈርዶስ አዱስ 19,404 እጩ የቦርድ አባል
12ኛ ብ/ጀ ሰለለሞን በየነ 11,022 እጩ የቦርድ አባል
13ኛ አቶ ዮሴፍ አሰፋ 10,200 እጩ የቦርድ አባል
14ኛ ወ/ሮ መቅደስ ገ/ፃዲቅ 1,572 እጩ የቦርድ አባል
በተጠባባቂነት የተያዙ
15ኛ ወ/ሮ አምሳል ካሳሁን 448 እጩ የቦርድ አባል
16ኛ ወ/ሮ ገነት አራጋው 134 እጩ የቦርድ አባል
ለ. ተፅእኖ ፈጣሪ ያልሆኑ ባለአክሲዮኖች (በተናጥል ጥቆማ) የተጠቆሙ እጩዎች ስም ዝርዝር
ደረጃ የእጩዎች ሙሉ ስም ያገኙት ድምፅ በአክሲዮን ብዛት ምርመራ
1ኛ ወ/ሪት ሜሮን ሰለሞን አፈሩ 7,148 እጩ የቦርድ አባል
2ኛ ጣና ኮሚኒኬሽን ኃ/የተ/የግ/ማ (በአቶ ወርቅነህ መኮንን ተወክሎ) 2,510 እጩ የቦርድ አባል
3ኛ ወ/ሮ ሀናን መሐመድ 560 እጩ የቦርድ አባል
4ኛ ወ/ሮ ኢማን አህመድ ኢብራሂም 560 እጩ የቦርድ አባል