አፍሪካ የልማት ዕርዳታ ማህበር የኢትዮጵያ ነዋሪዎች በጎ አድራጎት ደርጅት እ.ኤ.አ የ 2011-2014 በጀት ዓመት ሂሣቡን ለማስመርመር ይፈልጋል፡፡

Overview

  • Category : Auditing Related
  • Posted Date : 02/18/2023
  • Closing Date : 02/24/2023
  • Phone Number : 0930110041
  • Source : Reporter

Description

      የኦዲት ሥራ  ጨረታ ማስታወቂያ

አፍሪካ የልማት ዕርዳታ ማህበር የኢትዮጵያ ነዋሪዎች በጎ አድራጎት ደርጅት እ.ኤ.አ የ 2011-2014 በጀት ዓመት ሂሣቡን ለማስመርመር ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ የአዲት  ድርጅቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

  1. በህጋዊነት የተመዘገባችሁ፤ የታደሰ የንግድ እና የሙያ ማረጋገጫ ፈቃድ ያላችሁ፤
  2. የዘመኑን ግብር የከፈላችሁ፤
  3. በሂሣብ ምርመራ በቂ ሙያና የሥራ ልምድ ያላችሁ፤
  4. የታክስ መለያ ቁጥር (TIN Number) ያላችሁ፤

መሥፈርቱን የምታሟሉ ተወዳዳራዎች ሥራዉን ለማከናወን የምትጠይቁትን የገንዘብ መጠንና ሥራዉን አጠናቆ ለማስረከብ የሚፈጅባችሁን ጊዜ በመጥቀስ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ዉስጥ ከታች በተመለከተዉ አድራሻ የሙያ ደረጃችሁንና ህጋዊነታችሁን የሚገልፁ ማስረጃዎቻችሁን (የማይመለስ ፎቶ ኮፒዉን)  በመያዝ በሥራ ሰዓት ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

 አድራሻ፡ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09(በተለምዶ 02 ቀበሌ) የካ ጤና ጣቢያ አካባቢ፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0930110041/0910656918 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡