ኢማጅን ዋን ዴይ ኢንተርናሽናል ኦርጋናይዜሽን /imagine1day/ ኦሮሚያ እና በደቡብ ክልል በተለያዩ ወረዳዎች ላይ ለምንሰራው ፕሮጀክት Land Cruiser Hard top 10 setter ,5 door 2017-2020 Model መኪና ለ ሶስት ወር እና ሊቀጥል በሚችል በጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል

Imagin-Day-One-Logo-reportertenders

Overview

 • Category : Vehicle Rent
 • Posted Date : 09/18/2021
 • Phone Number : 0118697258
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 09/28/2021

Description

ቀን፡ 19/09/2021

የ COVID-19 መከላከያ እቃዎችን ፤ የጽህፈት መሳሪያዎችየትምህርት መርጃ መሳሪየዎችየላፕቶፕ እና ታብሌት ግዢ እንዲሁም የመኪና ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ

ኢማጅን ዋን ዴይ ኢንተርናሽናል ኦርጋናይዜሽን /imagine1day/ የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ የውጭ በጎ አድራጎት ድርጅት በትግራይ፤ በኦሮሚያ፣ እና በደቡብ ክልል በትምህርት ጥራት ማሻሻል ሥራ ላይ የበኩሉን አስተዋፅኦ እየሰጠ ይገኛል፡፡

በአሁኑ ጊዜም ድርጅታችን በኦሮሚያ እና በደቡብ ክልል በተለያዩ ወረዳዎች ላይ ለምንሰራው ፕሮጀክት Land Cruiser Hard top 10 setter ,5 door 2017-2020 Model መኪና ለ ሶስት ወር እና ሊቀጥል በሚችል በጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል በተጨማሪም የተለያዩ የ COVID-19 መከላከያ እቃዎችን፣ የጽህፈት አገልግሎት መሳሪያዎች፡ የትምህርት መርጃ መሳሪየዎች እና የላፕቶፕ እና ታብሌት እቃዎችን ግዢ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም፡-

 • ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉበት እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
 • የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ CPO ለ30 ቀናት የሚቆይ ከሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ከቫት ውጭ 2% ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለብቻ በታሸገ ፖስታ ማስያዝ የሚችሉ
 • ስለጨረታው የሚገልፀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) እና የታደሰ ንግድ ፈቃዳቸውን ማቅረብ ይኖርባቸዋል
 • ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ኢምፔሪያል አካባቢ ልዩ ስሙ 24 ከ ሜክሲኮ ኤምባሲ አጠገብ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና ፅሕፈት ቤት ከ መስከርም 10 2014 እስከ መስከረም 18 2014 ዓ/ም ባለው የስራ ሰዓት የጨረታ ዶክመንቶችን መግዛት ይችላሉ፡፡
 • የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ አንድ ኮፒ እና አንድ ኦርጂናል በማድረግ እና የጨረታ ማስከበሪያ ዎስትና ለብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ መስከረም 18 ቀን 2014 ዓ.ም ከ 8፡00 ሰዓት በፊት ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል
 • በሰም ካልታሸገ የጨረታው ሰነድ ተቀባይነት የለውም
 • ተጫራቾች ሁሉ ከዚህ ደብዳቤ ጋር የተያያዘውን ዝርዝር ዕቃዎች ዋጋ በመሙላት ጨረታው መስከረም 18 ቀን 2014 ዓ.ም 8:00 ሰዓት ላይ ራሳቸው ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው (በሰንዶች ማረጋገጫ የተረጋገጠ ህጋዊ ውክልና የያዙ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ኢምፔሪያል አካባቢ ልዩ ስሙ 24 ከ ሚክሲኮ ኤምባሲ አጠገብ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና ፅሕፈት ቤት ጨረታው ይከፈታል::
 • በድርጅት የውክልና ዳብዳቤ እንደማንቀበል በትህትና እንገልጻልን
 • ድርጅቱ ለተሻለ አማራጭ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ: – አዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ከ ሜክሲኮ ኤምባሲ አጠገብ

የቀጥታ ስልክ ቁጥር፡- 011 869 7258