ኢትስዊች አ.ማ በሁሉም የሃገራችን ባንኮችና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባለቤትነት የተመሰረተ ተቋም ሲሆን አ.ማህበሩ ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ህንጻ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ ማንኛውም በዘረፉ የተሠማራ አቅራቢ በጨረታው እንዲሳተፍ ይጋብዛል፡፡

Ethswitch-S.C-logo

Overview

 • Category : House & Building Purchase
 • Posted Date : 10/05/2022
 • Phone Number : 0115571204
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 10/20/2022

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ህንጻ ግዥ ጨረታ

የጨረታቁጥር NCB/Ets/039/2015

 1. ኢትስዊች አ.ማ በሁሉም የሃገራችን ባንኮችና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባለቤትነት የተመሰረተ ተቋም ሲሆን አ.ማህበሩ ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ህንጻ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ ማንኛውም በዘረፉ የተሠማራ አቅራቢ በጨረታው እንዲሳተፍ ይጋብዛል፡፡
 2. ለመወዳደር ፍቃደኛ የሆኑ ተጫራቾች ለዚሁ ግዥ የተዘጋጀውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ ከሐሙስ መስከረም 26 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የማይመለስ ብር 200 ( ሁለት መቶ ብር ) በኢትስዊች አካውንት ቁጥር A/C 01304030025600 አዋሽ ባንክ ወይም ንግድ ባንክ በአካውንት ቁጥር A/C 1000089578737 የድርጅታችሁን ስም አካታችሁ በማስገባት ክፍያውን ከፍለው ዘወትር በስራ ሰዓት መውሰድ ይችላሉ፡

ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት 2፡30-6፡00 እና ከሰዓት 6፡00 -11፡00 ሰዓት ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡00

 1. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ቴክኒክና እና ፋይናንስ የጨረታ ሰነዳቸውን እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ድረስ ከዚህ በታች በተጠቀሰው የካንፓኒው አድራሻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፤ ጨረታው ጥቅምት 10 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ይዘጋል፤ ከተጠቀሰው ሰዓት ዘግይቶ የሚመጣ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
 2. የቴክኒክ ሰነዱ ጥቅምት 10 ቀን 2015 ዓ.ም ጠዋት 5፡30 (ጨረታው በሚዘጋበት ቀን ) በካምፓኒው ዋና መ/ቤት በስነስርዓቱ መሳተፍ በሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
 3. ኢትሲዊች አ.ማ ካሳንቺስ ማርሻል ቲቶ ጎዳና ካሳንቺስ ሱፐር ማርኬት አካባቢ በሚገኘው ነጋ ሲቲ ሞል 4ተኛ (አራተኛ) ፎቅ ላይ ይገኛል፡፡
 4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን የቴክኒክና የፋይናንስ ሰነድ ለየብቻው ተለይቶ ለእያንዳንዱ ሠነድ ሁለት ኮፒ በማድረግ በግልፅ በሚታይ መልኩ የካንፓኒውን ስምና የህንፃ ግዥ ጨረታ መሆኑን በሚያሳይ ሁኔታ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
 5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በካንፓኒው በአካል በመገኘት ከላይ በተራ ቁጥር 3 በተጠቀሰው ቀን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 6. በተጫራቾች ለሚቀርበው ጨረታ ጨረታው ከተከፈተበት ዕለት አንስቶ እስከ 90 ( ዘጠና) ቀናት ድረስ የፀና ነው ፡፡
 7. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ጨረታ ብር 100,000.00 ( አንድ መቶ ሺ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ አ. ወይም የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል የሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታው ከሚፀናበት ጊዜ አንስቶ ለ 30 ( ሰላሳ ቀናት) የሚያገለግል መሆን አለበት ፡፡

ካንፓኒው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

ተጨማሪ ማብራሪያ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ ማግኘት ይቻላል፡፡

አቶ ታደለ ነጋሽ

ፋሲሊቲ ማኔጅመንት ኃላፊ

ስልክ ቁጥር ፡ +251-11-557 12 04,

ፋክስ+ 251-11-557 11 15

E-mail: tadelen44@gmail.com/ tadelen@ethswitch.com