ኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የአትሌቲክስ ማዘውተሪያ ስፍራ በለገጣፎ ለገዳዲ የአሸዋ ጥርጊያ ሜዳና አሸዋ ትራክ ግንባታ ስራ እና ዙሪያ አጥር ለማሳጠር ሚያስፈልጉ ግብዓቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Ethiopian-Athletics-Federation-logo

Overview

 • Category : Purchases
 • Posted Date : 11/14/2022
 • Phone Number : 0116479794
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 11/25/2022

Description

ህዳር 02/2015 ዓ.ም

ግልጽ የግንባታ ግብዓት ግልጽ ጨረታ ማታወቂያ

ኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የአትሌቲክስ ማዘውተሪያ ስፍራ በለገጣፎ ለገዳዲ የአሸዋ ጥርጊያ ሜዳና አሸዋ ትራክ ግንባታ ስራ እና ዙሪያ አጥር ለማሳጠር ሚያስፈልጉ ግብዓቶች ለመግዛት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ዕቃዎች ማለትም፡-

 1. ሽቦ ቁመቱ 2 ሜትር ርዝመቱ 800ሜትር
 2. ሲሚንቶ 120 ኩንታል
 3. አሸዋ 32 ሜትር ኩብ
 4. 02 ጠጠር 16ሜትር ኩብ
 5. 0 ጠጠር (ፊኖ) 10ሜትር ኩብ
 6. ፌሮ ብረት ባለ 8 ቁጥር 800 ቤርጋ
 7. ፌሮ ብረት ባለ 6 ቁጥር 150 ኪ.ግ
 8. ፕላውድ ባለ 18 ብዛት 8
 9. የፌሮ ማሰሪያ ሽቦ 20 ኪ.ግ
 10. ሚስማር የተለያዩ ቁጥሮች 10 ኪ.ግ
 11. የውሃ ማጠጫ ጎማ ባለ ¾ 100 በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

ህጋዊ የታደሠ የንግድ ስራ ፍቃድ፤ የቲንና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፤ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ 10,000.00 (አስር ሺ ብር) CPO አሰርቶ ማቅረብ፤ ጨረታውን ያሸነፈ ግለሰብ /አቅራቢ ድርጅት/ ግብዓቶቹን በራሱ ትራንስፖርት የሚያቀርቡ ሲሆን ተጫራች ከላይ የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የማያሟሉ ተጫራቾች ከውድድሩ ውጪ ይሆናሉ፡፡ ተጫራቾች ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት በአስር /10/ ተከታታይ የሥራ ቀናቶች ዘወትር በሥራ ሰዓት የመወዳደሪያ ዋጋቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ የኢትዮጵያ አትሌቲክሰ ፌዴሬሽን ሕንፃ 2 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6 ግዥና ፋይናንስ ደጋፊ ሥራ ሂደት ክፍል  የጨረታ ሰነዳቸውን እስከ 10ኛው ቀን እስከ ረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

ጨረታው በ10ኛው ቀን ከረፋዱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከረፋዱ 4፡30 ጉርድ ሾላ በሚገኘው በፌዴሬሽኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ስለ ጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ሲፈልጉ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ ስልክ በመደወል ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ፌዴሬሽኑ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- ጉርድ ሾላ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሕንጻ 2 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6

ለበለጠ መረጃ፡- 0116-47-97-94/ 0116-47-95-78 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ፋክስ 0116-45-08-79

ፖ.ሳ.ቁ.13336

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሸን