ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ. የካሣ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን ቀላል ከባድ እና ልዩ ልዩ የተሽከርካሪ አካላት ቅሪቶችን እንዲሁም የድርጅቱን ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Ethio-life-and-General-insurance-logo

Overview

 • Category : Vehicle Foreclosure
 • Posted Date : 10/22/2022
 • Phone Number : 0115549650
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 11/15/2022

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ

Ethio Life and General Insurance S.C

ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ. የካሣ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን ቀላል  ከባድ እና ልዩ ልዩ የተሽከርካሪ አካላት ቅሪቶችን እንዲሁም የድርጅቱን ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

 1. ተሽከርካሪዎቹን ለመግዛት በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ሁሉ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ከቸራሊያ ዝቅ ብሎ በሸዋ ዳቦ 350 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው የኩባንያው ተሽከርካሪዎች ማቆያ (Recovery Site) ከጥቅምት 14 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 25 ቀን 2015 ዓ.ም ባሉት የሥራ ቀናት በመምጣት ማየት ይቻላል፡፡
 2. ተጫራÓች ተሽከርካሪዎችን የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎኘ ከሰኞ ጥቅምት 14 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 25 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ባሉት የሥራ ቀናት ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ከመስቀል ፍላወር ወደ ደንበል በሚወስደው መንገድ ቶሊፕ ሆቴል ፊት ለፊት 5 ፎቅ በሚገኘው የኩባንያው ዋና መ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይቻላል፡፡
 3. ተጫራÓች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 10% በባንክ በተረጋገጠ ማዘዣ ለጨረታ ማስከበሪያ(CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
 4. የጨረታው አሸናፊዎች የተሽከርካሪውን ዋጋ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ የጨረታ ውጤት በተገለፀ በ10 ቀናት ውስጥ ከፍለው በ10 ቀናት ውስጥ ንብረቱን ከግቢው ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡
 5. የጨረታ ዋጋ ተንተርሶ ሌላ ዋጋ መስጠት አይቻልም፡፡ የጨረታ ዋጋ አባዝቶ ማቅረብ አይቻልም፡፡
 6. ተሽከርካሪው በጨረታ እስከተሸጠበት ድረስ የሚፈለግ ግብርና ታክስ ቢኖር ጨረታውን አሸንፈው የሚገዙ አይጠየቁበትም፡፡ ተሽከርካሪው ከተሸጠ በኋላ የሚፈለግ ግብር ታክስና እንዲሁም የቦሎ ክፍያና ተያያዥ ቢኖር የገዥው ኃላፊነት ይሆናል፡፡
 7. ተጫራÓች የሚያቀርቡት ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን የሚያጠቃልል መሆኑን በግልፅ ሁኔታ በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ካልተገለፀ በስተቀር ባቀረቡት ዋጋ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ተጨምሮ የሚታሰብ ይሆናል፡፡
 8. አሸናፊ ተጫራÓች ተሽከርካሪውን በራሳቸው ወጪ አስነስተው ይወስዳሉ፡፡
 9. ተጫራÓች ስለተሽከርካሪዎቹ መንገድ ትራንስፖርት በሰጠው ውሳኔና በጨረታው ሰነድ ላይ በተገለፀው መሠረት ከግምት ውስጥ በማስገባት ዋጋ መስጠት ይኖርባቸዋል፡፡
 10. ጨረታው ጥቅምት 26 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ኩባንያው ዋና መ/ቤት ይከፈታል፡፡ ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115549650/0911157195/0911153169 ደውለው መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡