ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ የባለአክስዮኖች 14ኛ ዓመታዊ መደበኛ እና 9ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባዔ

Ethio-life-and-General-insurance-logo

Overview

 • Category : Announcement
 • Posted Date : 11/06/2022
 • Phone Number : 0115549651
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 12/03/2022

Description

 ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ

 Ethio Life and General Insurance S.C. 

የባለአክስዮኖች 14 ዓመታዊ መደበኛ እና 9 ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባዔ

ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ የዋና መስሪያ ቤቱ አድራሻ፡ አዲስ አበባ ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 02 ፣የቤት ቁጥር 659 የሆነ የኩባንያው የተፈረመ ካፒታል ብር 191.6 ሚሊዮን፣ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለኩባንያው የተሠጠ የመድን ስራ ፈቃድ ቁጥር 013/08 ሲሆን ኩባንያው በኢትዮጵያ የንግድ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 አንቀፅ 366፣ 367፣ 370 እና 372 እንዲሁም በኩባንያው መመስረቻ ፅሑፍ መሰረት 14 ዓመታዊ መደበኛ እና 9 ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባዔውን ቅዳሜ ህዳር 24 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በአዲስ አበባ ኢንተር ሌግዤሪ ሆቴል የሚያካሂድ በመሆኑ ባለአክሲዮኖች ከላይ በተጠቀሰው ቀን፣ ቦታና ሰዓት በአካል ወይም በህጋዊ ወኪሎቻችሁ አማካኝነት ተገኝታችሁ በጉባዔው እንድትሳተፉ የዳይሬክተሮች ቦርድ በአክብሮት ጥሪውን ያቀርባል፡፡

ሀ. የባለአክስዮኖች 14 ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች

 1. እ.ኤ.አ በ2021/2022 የተደረጉ የአክሲዮን ዝውውሮችን ማፅደቅ፤
 2. እ.ኤ.አ የ2021/2022 የሒሳብ ዘመን የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፓርት ማድመጥ፤
 3. እ.ኤ.አ የ2021/2022 የሒሳብ ዘመን የውጭ ኦዲተሮች ሪፓርት ማድመጥ፤
 4. ከላይ በተራ ቁጥር 2 እና 3 በቀረቡት ሪፓርቶች ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
 5. እ.ኤ.አ የ2021/2022 የሒሳብ ዘመን የትርፍ ክፍፍል ላይ በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
 6. እ.ኤ.አ የ2021/2022 የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ የሥራ ዋጋን መወሰን፤
 7. እ.ኤ.አ የ2022/2023 የዳይሬክተሮች ቦርድ ወርሀዊ አበል ክፍያን መወሰን፤
 8. እ.ኤ.አ ከ2022/2023 ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ዓመታት የሚያገለግሉ የውጭ ኦዲተሮችን መሾም፤
 9. እ.ኤ.አ የ2022/2023 የውጭ ኦዲተሮችን የአገልግሎት ክፍያ መወሰን፤
 10. የዳይሬክተሮች ቦርድ የምልመላና አስመራጭ ኮሚቴ ሪፓርት ማድመጥ፤
 11. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫ ማካሄድ፤
 12. የ14ኛውን ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ቃለ-ጉባኤ ማፅደቅ፤

ለ. የባለአክስዮኖች 9 ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች

 1. በባለአክስዮኖች ተፈርሞ ያልተከፈለ የኩባንያው ካፒታል ተከፍሎ የሚጠናቀቅበትን ጊዜን መወሰን፤
 2. የኩባንያውን ካፒታል ማሳደግ እና ካፒታሉን ለማሳደግ በቀረበው የእቅድ መርሀ ግብር ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
 3. የባለአክስዮኖች 9 ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ ቃለ-ጉባኤን ማፅደቅ፤

ማሳሰቢያ

 • በስብሰባው ላይ መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች በንግድ ሕግ አንቀፅ 373 እና 377 መሰረት ጉባዔዎቹ ከሚካሄዱበት ዕለት ሶስት ቀናት በፊት በመስቀል ፍላወር አከባቢ በሚገኘው በኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ ሕንፃ ዋና መስሪያ ቤት 4 ፎቅ ላይ በመቅረብ ለዚሁ ዓላማ የተዘጋጀውን የውክልና ቅፅ ሞልተው በመፈረም በተወካዮቻቸው አማካኝነት ጉባኤውን መሳተፍ እንደሚችሉ በአክብሮት እንገልፃለን፡፡
 • የኩባንያው ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባኤው ለመሳተፍ ሲመጡ ኢትዮጵያዊ ዜግነታቸውን የሚያሳይ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ በመያዝ በጉባኤው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡ እንዲሁም ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ሆነው የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው የኩባንያው ባለአክሲዮኖች ትውልደ ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መታወቂያ/ቢጫ ካርድ ይዘው መቅረብ እንዳለባቸው በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
 • የውክልና ቅጹን በዋና መ/ቤት መጥተው ያልሞሉ ባለአክሲዮኖች ህጋዊ ተወካዮች ስብሰባውን መካፈል የሚያስችል ግልፅ ስልጣን የሚያሳይና በሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ቢሮ ወይም አግባብ ባለው አካል የተመዘገበ ውክልና ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 • የስብሰባው ተሳታፊዎች የጤና ሚኒስቴር ያወጣው የኮቪድ 19 መከላከያ መንገዶችን በጥብቅ መተግበር ይኖርባቸዋል፡፡

በዳይሬክተሮች ቦርድ ትእዛዝ

ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ

+251-011-5549651 +251-011-5571781

አዲስ አበባ‚ ኢትዮጵያ