ኢትዮ ኒፖን ቴክኒካል ካምፓኒ አ.ማ. ለኤክስፖርት የተቀመጠ 2765.7 ኩንታል (ደሲ) ሽንብራ ባለበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : Other Sale
 • Posted Date : 09/24/2022
 • Phone Number : 0115514661
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 10/03/2022

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ኢትዮ ኒፖን ቴክኒካል ካምፓኒ አ.ማ. ለኤክስፖርት የተቀመጠ 2765.7 ኩንታል (ደሲ) ሽንብራ ባለበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ከታች የተዘረዘሩትን ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላት በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚቻል መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡

 1. ስለጨረታው አፈጻጸም ዝርዝር መረጃ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) ብር በመክፈል ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 23 ቀን 2015 ዓ.ም. ከቀኑ 3፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛትና ማስገባት ይችላሉ፡፡
 2. እያንዳንዱ ተጫራች የታደሰ የንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይነት ሰርተፊኬት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለበት፡፡
 3. እያንዳንዱ ተጫራች የሚሰጠውን የመወዳደሪያ ዋጋ 1/4ኛ የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ (CPO) በኢትዮ-ኒፖን ቴክኒካል ካምፓኒ አ.ማ. ስም አሰርቶ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
 4. ያለ ጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
 5. እህሉን ሀና ማርያም በሚገኘው ዓለም ኢንተርናሽናል እና አቃቂ በሚገኘው የቀጭን አምባ መጋዘን በመገኘት ማየት ይቻላል፡፡
 6. ጨረታው መስከረም 23 ቀን 2015 ዓ.ም. ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አፍሪካ ህብረት የስብሰባ አዳራሽ ፊት ለፊት በሚገኘው በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡ ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመወዳደሪያ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
 7. የጨረታው አሸናፊ የጨረታው ውጤት ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 3 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ክፍያ ፈጽሞ እህሉን መረከብ ይኖርበታል፡፡ ይህ ካልሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ በማድረግ ጨረታው ይሰረዛል፡፡
 8. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር

0115-51-46-61/0115-51-45-76

ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡