ኢኳቶሪያል ቢዝነሰ ግሩፕ ኃ.የተ. የግ. ማህበር የጽሕፈት መሣሪያዎች እና ጥቃቅን የቢሮ መገልገያ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

equatorial-business-group-logo

Overview

 • Category : Stationery Supplies
 • Posted Date : 11/19/2022
 • Phone Number : 0114400102
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 12/07/2022

Description

 ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር 03/2015

ኢኳቶሪያል ቢዝነሰ ግሩፕ .የተ. የግ. ማህበር የጽሕፈት መሣሪያዎች እና ጥቃቅን የቢሮ መገልገያ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት በጨረታው ላይ መወዳደር ለምትፈልጉ ተጫራቾች፡

 1. በዘርፉ ሕጋዊ የሆነ የታደሰ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉበት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
 2. የግዥ እና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ባዘጋጀው የዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና በተወዳደሩበት የጨረታሰነድ ላይ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
 3. ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠና በጨረታ ላይማሳተፍ የሚያስችል የዕቃ አቅራቢነት ማስረጃ ደብዳቤ/ ማቅረብ አለባቸው፡፡
 4. ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin No) የሚገልጹ የምስክርወረቀት ኮፒውን ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 5. ተጫራቾች የሚጫረቱበት የዕቃዎች ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ በሚታይ መልኩ ያለስርዝ ድልዝበመሙላት የሞሉት ዋጋ በኢትዮጵያ ብር ሆኖ ቫት ጨመሮ መሆን አለበት፡፡
 6. ተጫራቾች በገዙት ጨረታ ሰነድ በሁሉም ገጽ ላይ የድርጅቱ ባለቤት ፊርማ፣ ሙሉ አድራሻውንና ሕጋዊ ማህተም ያረፈበትኦሪጅናሉን በፖስታ በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (BID BOND) ከባንክ በተረጋገጠ (CPO)የአጠቃላይ የጨረታውን ዋጋ 2% (ሁለት በመቶ) ለብቻ እንዲያቀርቡ ይጠበቃልከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማስገባት አለባቸው እንዲሁም    

እያንዳነዱ ዕቃ አይነት (sample) ማቅረብ አለባቸው፡፡

 1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር) በመከፈል ይህ ማስታወቂያበሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን ከድርጅቱ ግዥ እና አቅርቦት ቢሮ 1 ፎቅ ከከበድ ተሸከርካሪ ቢዝነሰ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
 2. ጨረታው 16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ህዳር 8, 2015 ከጠዋቱ 500 ሰዓት ላይ የጨረታ ሣጥኑ ተዘግቶ ህዳር 28, 2015 ቀን ከጠዋቱ  500 ሰዓት ላይይከፈታል፡፡ በጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት ተጫራቾችም ሆኑ ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡
 3. የጨረታ መከፈቻው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ላይ ተዘግቶ የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን።
 4. ተጫራቾች አንድ ተጫራች የሰጠውን ዋጋ ለይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት የተከለከለ ነው፡፡
 5. ኩባንያዉ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡

13.አድራሻ ኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ አቃቂ ቃሊቲ ክፍል ከተማ ወረዳ 06 የቢት ቁጥር 402 ሳሪስ አቦ  ሆራይዞን ጎማ አጠገብ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና /ቤት (VOLVO).         ስልክ ቁጥር 0114-400102 ወይም 0114-406218 አዲስ አበባ፡