ኤደን ቢዝነስ አ/ማህበር ግንባታው ሙሉ ለሙሉ ከተጠናቀቀ ህንጻ ዉስጥ 5ኛ-8ኛ ፎቅ ላይ የሚገኙትን መኖሪያ ቤቶች በዝግ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Eden-business-s.c-Logo

Overview

  • Category : House & Building Sale
  • Posted Date : 04/19/2021
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 05/04/2021

Description

የመኖሪያ ቤት ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

ኤደን ቢዝነስ አ/ማህበር ንብረትነቱ የድርጅቱ የሆነ ለንግድ፣ ለቢሮ እና ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውል ህንጻ አጠቃላይ የመሬቱ ስፋት 250 ካ.ሜ. ህንፃው ያረፈበት 182 ካ.ሜ. የሆነ 1 ቤዝመንት እና ግራውንድ+ 7 እና ቴራስ ያለዉ ሆኖ ግንባታው ሙሉ ለሙሉ ከተጠናቀቀ ህንጻ ዉስጥ 5ኛ-8ኛ ፎቅ ላይ የሚገኙትን መኖሪያ
ቤቶች በዝግ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

1.ከ5 ኛ እስከ 7ኛ ያሉት መኖሪያ ቤቶቹ በአንድ ወለል ሁለት ሲሆኑ አንዱ ባለ አንድ መኝታ ክፍል የወለል ስፋቱ 75.85 ካ.ሜ. ፤ እንዲሁም ባለ ሁለት መኝታ ክፍል የወለል ሥፋቱ 100.3 ካ.ሜ. ነው፡፡ 8ኛ ወለል ላይ የሚገኘዉ ባለ አንድ መኝታ ሆኖ ሥፋት 76 ካ.ሜ. ላይ ያረፈ ነዉ፡፡2. ሕንጻው ለጋራ መጠቀሚያ የሚውል ሥፍራ ቴራስ ላይ እና ቤዝመንት ላይ ለተሸከርካሪዎች ማቆሚያ /ፓርኪንግ/ አለው፡፡
3. ህንጻውን በግንባር ማየት ለሚፈልግ አድረሻው በአዲስ አበባ ከተማ፣ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 የቤቱ ቁጥር አዲስ የሆነ ከሲግናል ወደ መገናገኛ በሚወስደው መንገድ የሾላ ትራፊክ መብራት ከመድረሱ 100 ሜትር በፊት በግራ በኩል ታጥፎ ዘወትር በሥራ ሰዓት ቀርቦ ማየት ይቻላል፡፡
4. ጨረታው የሚቆይበት ጊዜ ከሚያዝያ 11 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 26 ቀን 2013 ዓ.ም. እስከ ጠዋቱ 4 ሰዓት ድረስ ይሆናል፡፡ ጨረታዉ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 5.00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ደግሞ ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል፡፡
5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል የተጫራቾች አድራሻ መግለጫን በማካተት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በድርጅቱ ዋና ቢሮ 2ኛ ወለል ግዥ ክፍል በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
6. የጨረታዉ መነሻ ዋጋ ለአንድ ካሬ ብር 43000.00 (አርባ ሶስት ሺ) ነዉ፡፡
7. ድርጅታችን ሌላ የተሸለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡