ኤ/ኤን/ደብሊው/አር የገበያ ማዕከል አክሲዮን ማህበር ጥር 7 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ የመደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ተጠርቷል፡፡

Overview

  • Category : Announcement
  • Posted Date : 12/28/2022
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 01/15/2023

Description

ጉዳዩ፡- የማህበሩ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ላይ እንዲገኙ መጥራትን ይመለከታል

ማህበራችን ኤ/ኤን/ደብሊው/አር የገበያ ማዕከል አክሲዮን ማህበር ጥር 7 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ የመደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ተጠርቷል፡፡

ስብሰባው የማህበሩ 7ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ሲሆን የስብሰባው አጀንዳዎች፡-

1 የ2014 ዓ/ም የአስተዳዳሪዎች ቦርድ የስራ አፈጻጸም ሪፖርትና የማህበሩን የሂሳብ

ሪፖርት መርምሮ ማጽደቅ

2 የትርፍ ክፍፍልን (ዴቪደንድ) በተመለከተ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፍ

3 የማህበሩን ካፒታል ማሳደግ በተመለከተ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፍ

4 በቀጣይ ለማህበሩ ህንጻ ግንባታ ገቢ ማመንጨትን በተመለከተ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፍ

5 የ2014 ዓ/ም በጀት አመት የውጭ ኦዲት ሪፖርት ማድመጥና ማጽደቅ

6 በህንጻው ላይ የሚሰራውን አፓርትመንት በተመለከተ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፍ

7 በህንጻው ላይ የተሰሩ ሱቆችና የምድር በታች ግንባታዎች የማጠናቀቂያ (ፊኒሺንግ) ስራ በተመለከተ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፍ

8 ተሻሽሎ በቀረበው መመስረቻና መተዳደሪያ ጹሁፍ በተመለከተ መርምሮ እና ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፍ

9 የማህበሩ አባላት ሱቅ ተሸንሽኖ በስማቸው ካርታ የሚሰጥበትን ሁኔታ በተመለከተ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፍ

መሆናቸውን እየገለጥን በእለቱ ማንነትዎን የሚገልጥ መታወቂያ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ በመያዝ በማህበሩ ህንጻ በተዘጋጀው የመሰብሰቢያ ቦታ በመገኛት ወይም በወካይ የሚወከሉ ከሆነ ከስብሰባው ሁለት የስራ ቀናት በፊት ሱማሌ ተራ ተክለሃይማኖት ሆስፒታል ፊት ለፊት ግሎባል ኢንሹራንስ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 26 ራስዎ ወይም ተወካይዎ የውክልና ኦርጂናልና ፎቶ ኪፒ ይዘው በመቅረብ እንዲያስመዘግቡና በጉባኤ እንዲሳተፉ ጥሪ እናደርጋለን፡፡

ማሳሰቢያ

  • ተወካይ የሚያቀርበው የውክልና ሰነድ በአክሲዮን ማህበር ስብሰባ ላይ መሰብሰብ፣ድምፅ መስጠት፣በቃለ ጉባኤ ላይ መፈረም እና ከላይ በተመለከቱት አጀንዳዎች ላይ ውሳኔ ማሳለፍ የሚችል መሆኑን እርግጠኛ እንዲሆኑ
  • መታወቂያና ውክልና ኦርጂናልና ፎቶ ኮፒ ይዘው እንዲቀርቡ እናሳስባለን ፡፡
  • የጠቅላላ ጉባኤው ውሳኔዎች በስብሰባው ባልተሳተፉትም ላይ አስገዳጆች ናቸው፡፡