እናት ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/90 መሰረት የተረከበውን ንብረት ከዚህ በታች በሰንጠረዠ ላይ የተገለጸውን መኖሪያ ቤት ባለበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Enat-Bank-logo-reportertenders

Overview

 • Category : House & Building Foreclosure
 • Posted Date : 08/06/2022
 • Phone Number : 0115585014
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 08/25/2022

Description

እናት ባንክ ..

­­­­­­­­­­­­­­­­­­­­­­­­­­­­­ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የንብረት ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡እባ/ንማ/05/2014

እናት ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/90 መሰረት የተረከበውን ንብረት ከዚህ በታች  በሰንጠረዠ ላይ የተገለጸውን  መኖሪያ ቤት ባለበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ስለሆነም ፍላጎት ያላቸውን ተጫራቾች ከታች በቀረቡት ማብራሪያዎች መሰረት በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡

. የቦታው አገልግሎት ለጨረታ የቀረበው ንብረት የሚገኝበት አድራሻ  

የንብረት አይነት

የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር የቦታው ስፋት የጨረታ መነሻ ዋጋ
1 ለመኖሪያ ሰንዳፋ በኬ ቪላ ቤትና ሰርቪስ ቤቶች LHC no 658/3394/97 300 ሜትር.ካሬ 2,050,000.00

ማሳሰቢያ

 • ለጨረታ የቀረበውን ንብረት ለማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ዋጋቸውን ከማቅረባቸው በፊት ከባንኩ ጋር አስቀድመው ቀጠሮ በመያዝ ማየት ይችላሉ፡፡
 • ተጫራቾች የጨረታ አካሄድ ዝርዝር መመሪያ የያዘውን ሠነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ካዛንችስ እናት ታወር ላይ በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 6ኛ ፎቅ የግዥ እና ፋሲሊቲ ስራ አመራር መምሪያ በመቅረብ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡
 • ተጫራቾች የንብረቱን የጨረታ መነሻ ዋጋ 10% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ (ሲ.ፒኦ) ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 • ተጫራቾች ንብረቱን ለመግዛት የሚሰጡትን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ካሰፈሩ በኃላ የጨረታ ማስከበሪያና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን በማያያዝ ካዛንችስ እናት ታወር ላይ በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት 6ኛ ፎቅ የግዥ እና ፋሲሊቲ ስራ አመራር መምሪያ ዘወትር በስራ ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ እስከ ነሐሴ 19 ቀን 2014 ዓ.ም. እስከ ጠዋቱ 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 • ጨረታው ሐሙስ ነሐሴ 19 ቀን 2014 ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባንኩ ዋና መ/ቤት 7ኛ ፎቅ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
 • የጨረታው አሸናፊ ሊዝ እና ንብረቱን በማስተላለፍ ሂደት ለመንግስት የሚከፈለውን ማናቸውም ክፍያዎች ይከፍላል፡፡
 • የጨረታው አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ዋጋ በሙሉ የጨረታው አሸናፊ መሆኑ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ አጠናቆ መክፈል ይኖርበታል፡፡
 • ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
 • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-5585014 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡

እናት ባንክ ..