ኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ አ.ማ ከባለዕዳዎች ለሚፈልገው ገንዘብ በዋስትና የያዘውንና ከዚህ በታች በሠንጠረዡ የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/1990 እንደተሸሻለ ለባንኮች በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ንብረቶቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Cooperative-Bank-of-Oromia-S.C-Log

Overview

 • Category : House & Building Foreclosure
 • Posted Date : 07/17/2022
 • Phone Number : 0921205516
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 08/18/2022

Description

ኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ አ.ማ ከባለዕዳዎች ለሚፈልገው ገንዘብ በዋስትና የያዘውንና ከዚህ በታች በሠንጠረዡ የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/1990 እንደተሸሻለ ለባንኮች በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ንብረቶቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ተጫራቾች ለጫረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች በመገንዘብ ማክበር ይኖርባቸዋል፡፡

 1. ጨረታውን በድርጅት ስም የሚጫረት ተጫራች በዘመኑ የታደሰ የንግድ ምዝገባ ወረቀት፣ የንግድ ፍቃድና ከድርጅቱ የተሰጠዉ ውክልና ማቅረብ አለበት:: ማንኛውም ተጫረች የታደሳ መታወቂያ ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
 2. ተጫራቾች ጨረታው በሚካሄድበት ዕለት የጨረታውን መነሻ ዋጋ ¼ (25%) የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በባንክ ክፍያ ማዘዣ ሲፒኦ በኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ አ.ማ ስም አሰርተው ወይንም በጥሬ ገንዘብ ይዘው በመቅረብ ንብረቱ በሚገኝበት አድራሻ ቀርበው በመመዝገብ በጨረታው ለመሳተፍ ይችላሉ፡፡
 3. ጨረታው ከታች ቀንና ሰዓቱ በተገለጸው መሠረት ባለዕዳዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ለጨረታ የቀረቡት ንብረቶች በሚገኙበት ቦታ ይካሄዳል፤ ባለዕዳዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ሳይገኙ ቢቀሩ ግን ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል፡፡
 4. ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት መጎብኘት ለሚፈልጉ ተጫራቾች የኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ባንክ አ.ማ ሸረሮ  ቅርንጫፍ ሸረሮ ከተማ ያለውን  እና ኡታዋዩ ቅርንጫፍ በሻሻመኔ ከተማ ያለውን ያስጎበኛል:: ለተጨማሪ መረጃ  ሸረሮ ቅርንጫፍ  በስልክ ቁጥር 011-133-09-34፣ ወይም 0921-20-55-16 ኡታዋዩ ቅርንጫፍ በስ.ቁ 046-110-12-56/3998 ወይንም  0912-86-25-12 ላይ በመደወል መጠየቅ ይቻላል::
 5. የጨረታው አሸናፊ የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል አለበት፤ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ተሰርዞ አዲስ የሐራጅ ማስታወቅያ ወጥቶ የሚካሄድ ይሆናል፡፡
 6. በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ወይንም ጥሬ ገንዘብ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረጋል::
 7. የጨረታው አሸናፊ በሕጉ መሠረት የሚከፈለውን ማናቸውንም ክፍያ ቫትን ጨምሮ እና የስም ማዛወሪያ ከፍሎ ስሙን ወደ እራሱ ያዛውራል፡፡
 8. ባንኩ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡
ተቁ

 

 

 

የተበዳሪው ስም

 

የንብረት አስያዥ ስም

 

የንብረቱ ዓይነት

አበዳሪው ቅርንጫፍ  

ለጨረታ የቀረበው ንብረት አድራሻና ዝርዝር ሁኔታ

የቦታ ስፋት በካ/ሜ  

የጨረታ መነሻ ዋጋ

 

ጨረታው የሚካሄድበት ቀን፣ሰዓትና ቦታ

 

ዞን

 

ወረዳ

 

ከተማ

 

ቀበሌ

የቤት

ቁጥር

 

የካርታ/ቁ

1  

ሸረሮ ቢዝነስ ዲቬሎፕመንት ኃ/የተ/የግ/ማ

 

ሸረሮ ቢዝነስ ዲቬሎፕመንት ኃ/የተ/የግ/ማ

ለወተት ተወጾ

ልማትና ከብት

እርባታ አገልግሎት

 

ሸረሮ

 

ሰሜን ሸዋ

 

ደብረ

ሊባኖስ

 

ሸረሮ

 

01

 

አዲስ

 

802/2001

 

5000

 

938,989.27

ነሐሴ 12 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-6፡00 በደብረ ሊባኖስ ወረደ ሸረሮ ከተማ ቀበሌ 01 ቤቱ በሚገኝበት ቅጥር ግቢ ውስጥ ይካሄዳል፡፡
2  

ዱሬሳ ምደቅሣ

በጥዬ

 

ዱሬሳ ምደቅሣ

በጥዬ

 

የንግድ ሕንጻ

ኡታዋዩ

 

 

ምዕ/አርሲ

 

ሻሸመኔ

 

ሻሸመኔ

 

አቦስቶ

 

 

14175

 

1064.77

 

5,933,273.87

ነሐሴ 13 ቀን 2014 ዓ.ም  ከጠዋቱ 4፡00-6፡00 ሻሸመኔ ከተማ አቦስቶ ቀበሌ የንግድ ቤቱ በሚገኝበት ቅጥር ግቢ ውስጥ ይካሄዳል፡፡

                                          የኦሮሚያ  ህብረት  ሥራ  ባንክ  አ.ማ