ኦሮሚያ ባንክ አ.ማ በአዲስ የተተኩ የየቅርንጫፎቹን የስም ማስታወቂያ ሰሌዳ በጨረታ በማወዳደር ባሉበት ቦታ እና ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Oromia-international-bank-logo-1

Overview

  • Category : Billboards & Digital Advertising
  • Posted Date : 11/14/2022
  • Phone Number : 0115572037
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 11/24/2022

Description

የ ጨረታ ቁጥር: ግፋዳ /አፋማ/001/2015

ያገለገሉ ዕቃዎች የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2015

ኦሮሚያ ባንክ አ.ማ ቀደም ሲል የነበረውን ሎጎ(Logo) በመቀየሩ ምክንያት በቅርንጫፎች ላይ የነበሩት ከ300 በላይ የሚሆኑ የቀድሞ የስም ማስታወቂያ ሰሌዳ(Light Box) በአዲስ እየተተካ ይገኛሉ፡፡ በመሆኑም እነዚህን በአዲስ የተተኩ የየቅርንጫፎቹን የስም ማስታወቂያ ሰሌዳ በጨረታ በማወዳደር ባሉበት ቦታ እና ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ዕቃውን መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል ለዚሁ የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ ቦሌ መንገድ ጌቱ ኮሜርሽያል ሴንተር ጎን ከሚገኘዉ የባንኩ ዋና መ/ቤት 9ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 407-9-3 በመውሰድ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች ለጨረታው ናሙና የቀረቡትን ያገለገሉ የቅርንጫፎች የስም ማስታወቂያ ሰሌዳ ገርጂ አካባቢ ከሚገኘው የባንኩ መጋዘን በአካል ተገኝተው በማየት ዋጋቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ እስከ ህዳር 15 ቀን 2015 ዓ/ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ ከላይ በተገለፀዉ የባንኩ ዋና መ/ቤት አድራሻ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች ለጨረታው የቀረቡትን ንብረቶች ከየቅርንጫፎቹ በሚፈቱበት ወቅት በመገኘት ይረከባሉ
  3. ጨረታዉ በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 8፡00  ላይ ተዘግቶ 8፡30 ሰዓት ላይ በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት መገኘት በሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ፊት ይከፈታል፡፡
  4. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡

ኦሮሚያ ባንክ አ.ማ

መደበኛ ስልክ ቁጥር:- 0115-57-20-37/96 0116-67-16-85

ተንቀሳቃሽ ስልክ ቁጥር፡- 0912-73-64-32/0913-46-99-87/0911-69-53-48