ኦሮሚያ ባንክ የሐራጅ ሽያጭ ውጤት ስለማሳወቅ
Overview
- Category : Announcement
- Posted Date : 02/18/2023
- Closing Date : 03/06/2023
- Source : Reporter
Description
የሐራጅ ሽያጭ ውጤት ስለማሳወቅ
ለ:- አቶ አልሰን ፍሮምሳ ስፉ
ባሉበት
የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ ተበዳሪ የሆኑት ወ/ሮ ወርቅነሽ አመሣ ኤጀርሳ ከባንኩ ኦዳ ቅርንጫፍ የወሰዱትን ብድር በውሉ መሰረት መክፈል ባለመቻላቸው ለብድሩ ዋስትና እንዲሆን በመያዣነት የተያዘው በተበዳሪዋ ሥም በካርታ ቁጥር BMO 530/2000 ተመዝግቦ በምዕ/ሸዋ ዞን፣ ኦሎንኮሚ ከተማ ውስጥ የሚገኘው የንግድ ህንጻ በጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 5,533,458.06 እንዲሸጥ መወሰኑ ይታወቃል፡፡ በዚሁ መሰረት ታህሣሥ 23 ቀን 2015 ዓ.ም በሪፖርተር ጋዜጣ ለሶስተኛ ጊዜ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ ወጥቶ የጨረታ ኮሚቴ አባላት እንዲሁም ታዛቢዎች በተገኙበት በቀን 26/05/2015 ዓ.ም በኦሮሚያ ባንክ ጊንጪ ቅርንጫፍ ውስጥ በተካሄደው ጨረታ ንብረቱን ለመግዛት ከቀረቡት ሶስት ተጫራቾች ከፍተኛ ዋጋ የሆነውን ብር 15,000,000.00 (አሥራ አምስት ሚሊዮን ብር) በማቅረቦ አሸናፊ መሆኖን የባንኩ የብድር አፅዳቂ ኮሚቴ እ.ኤ.አ በቀን 13/02/2023 (06/06/2015 ዓ.ም) ያፀደቀሎት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ስለሆነም ያሸነፉበትን ዋጋ ብር 15,000,000.00 (አሥራ አምስት ሚሊዮን ብር) እና ለመንግስት የሚከፈለው ተጨማሪ እሴት ታክስ 15% ብር 2,250,000.00 በድምሩ ብር 17,250,000.00 (አስራ ሰባት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሃምሳ ሺ ብር ) ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በአስራ አምስት (15) ቀናት ውስጥ አጠቃለው ለባንኩ ኦዳ ቅርንጫፍ ገቢ እንዲያደርጉ እና ንብረቱን እንዲረከቡ እያሳሰብን በተገለፀው የጊዜ ገደብ ውስጥ ክፍያውን አጠቃለው የማይከፍሉ ከሆነ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለባንኩ ገቢ እንደሚሆን ጭምር እናሳስባለን፡፡
በተጨማሪም ንብረቱ እንደገና ለጨረታ ቀርቦ እርሶ ካሸነፉበት ዋጋ ባነሰ ከተሸጠ ባሸነፉበት ዋጋ እና በቀጣዩ ጨረታ በቀረበው ዋጋ መካከል ያለውን የገንዘብ ልዩነት ወይም ተጫራች ሳይገኝ ቀርቶ ባንኩ በአዋጅ ቁጥር 97/90 አንቀጽ 3 እና 216/92 አንቀጽ 2 መሰረት ንብረቱን የሚወርስ ከሆነ ከጨረታ መነሻ ዋጋው ጋር ያለውን የዋጋ ልዩነት እና በዚህም ምክንያት በባንኩ እና በተበዳሪዋ ላይ ለሚደርስ ማንኛውም ኪሣራ በህግ ተጠያቂ የሚሆኑ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ኦሮሚያ ባንክ