ኦሮሚያ ኢንሹራንስ አ.ማ የሙሉ ውድመት ካሣ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን ተሽከርካሪዎችን፣ የተሽከርካሪ አካላት እና ሌሎች ቁሳቁሶችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ቅዳሜ ሰኔ 04 ቀን 2014 ዓ.ም ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Oromia-Insurance-Company-logo-1

Overview

 • Category : Vehicle Foreclosure
 • Posted Date : 05/30/2022
 • Phone Number : 0115589676
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 06/11/2022

Description

Inshuraansii Oromia (W.A)

  ኦሮሚያ ኢንሹራንስ  .

Oromia Insurance S.C

የጨረታ ማስታወቂያ

ኩባንያችን የሙሉ ውድመት ካሣ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን ተሽከርካሪዎችን፣ የተሽከርካሪ አካላት እና ሌሎች ቁሳቁሶችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ቅዳሜ ሰኔ 04 ቀን 2014 ዓ.ም ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ተሽከርካሪዎቹ እና ሌሎች ቁሳቁሶችን በሚገኙበት ቃሊቲ መናኸሪያ ለመድረስ 100 ሜትር ሲቀረው ሸዋ ዳቦ ጀርባ ከቃሊቲ የእንስሳት መኖ ድርጅት ዝቅ ብሎ ሰለሞን ብሎኬት ማምረቻ አጠገብ በሚገኘው የኩባንያችን ሪከቨሪ ቅጥር ግቢ ውስጥ ከግንቦት 22 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ሰኔ 03 ቀን 2014 ዓ.ም በመመልከት የሚጫረቱበትን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 50.00 በመክፈል ኦሮሚያ ኢንሹራንስ ዋና መ/ቤት ከወሎ ሰፈር ወደ ጐተራ ማሳለጫ  በሚወስደው መንገድ ቴሌ ማሰልጠኛ አለፍ ብሎ ድሬደዋ ህንፃ አጠገብ  መግዛት የምትችሉ ሲሆን ጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ቀን ሰኔ 02  እና ሰኔ 03 ቀን 2014 ዓ.ም መሆኑን እየገለጽን፣ በተጠቀሱ የጨረታ ማስገቢያ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ሰነዱን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማሸግ ዋና መ/ቤታችን ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገቢ በማድረግ መጫረት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ማሳሰቢያ

 • ጨረታው በኩባንያው ዋና መ/ቤት ህንፃ 3ኛ ፎቅ በሚገኘው የኩባንያው የሥልጠና አዳራሽ ቅዳሜ ሰኔ 04 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት የውስጥ ኦዲት አገልግሎት እና ተጫራቾች ወይም የተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
 • ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት የተከለከለ ነው፡፡
 • ተጫራቾች ለተሽከርካሪ የሚጫረቱ ከሆነ ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 15% በባንክ ክፍያ ማስያዣ (CPO) በታሸገ ኢንቨሎፕ ከነዋጋው ማስገባት የሚጠበቅባቸው ሲሆን ነገር ግን የተሽከርካሪ አካላት እና ሌሎች ቁሳቁሶች የሚጫረቱ ከሆነ የጨረታ መነሻ ዋጋቸውን መሠረት በማድረግ ኩባንያችን ባስቀመጠው ዝርዝር መሠረት የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
 • ከቀረጥ ነፃ ከሆኑ ተሽከርካሪዎች በስተቀር ለሌሎች ተሽከርካሪዎች ከጨረታው በፊት ዕዳዎች ቢኖሩ በኩባንያው ይሸፈናሉ፡፡ ሆኖም ግን ከጨረታ በኋላ ያሉትን ማንኛውንም ወጪዎች በሙሉ ገዢው ይሸፍናል፡፡
 • የጨረታ አሸናፊዎች ያሸነፉበት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15% (አስራ አምስት በመቶ) በተጨማሪ ይከፍላሉ፡፡
 • የጨረታው ውጤት የኩባንያው የማስታወቂያ ቦርድ እና ድረ ገጽ ላይ የሚገለጽ ሲሆን፣ ውጤቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ እስከ አስር (10) ቀናት ውስጥ ድረስ አሸናፊዎች ክፍያ ፈጽመው ንብረቶቹን ካልተረከቡ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለኩባንያው ገቢ ይደረጋል፡፡
 • የተለያዩ የተሽከርካሪ አካላት እና ቁሳቁሶችን የሚጫረቱ እና አሸናፊ የሚሆኑ በምድብ የተቀመጡትን ዕቃዎች ከኩባንያው ግቢ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ወጪ የማድረግ ግዴታ አለባቸው ፡፡
 • ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 11 68 73 41 ወይም 011-5-58-96-76 በመደወል ማነጋገር ይችላሉ፡፡

ኦሮሚያ ኢንሹራንስ  አ.ማ

ዋና መ/ቤት አድራሻ

ከወሎ ሰፈር ወደ ጐተራ ማሳለጫ በሚወስደው ዋና መንገድ (ኢትዮ-ቻይና መንገድ)   ከኢትዮ-ቴሌኮም ማሰልጠኛ አጠገብ

ስልክ ቁ.  0115 –  58 96 76

         0115 –  57 21 21