ኦሮሚያ ኢንሹራንስ (አ.ማ) የባለአክሲዮኖች 13ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ

Oromia-Insurance-Company-logo

Overview

 • Category : Announcement
 • Posted Date : 11/07/2022
 • Phone Number : 0115572121
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 01/08/2023

Description

የባለአክስዮኖች 13 መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ የጥሪ ማስታወቂያ

ኦሮሚያ ኢንሹራንስ (አ.ማ) የባለአክሲዮኖች 13 መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ታህሳስ 01 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ በሂልተን ሆቴል ይካሄዳል፡፡ ስለሆነም የኩባንያው ባለአክሲዮኖች በተጠቀሰው ቦታ፣ ቀንና ሰዓት እንድትገኙ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

የ13 መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች

 1. የጉባዔውን ድምጽ ቆጣሪዎች መሰየምና ምልዓተ ጉባዔ መሟላቱን ማረጋገጥ፣
 2. የጉባዔውን አጀንዳ ማጽደቅ፣
 3. የአዳዲስ አክሲዮን ሽያጭና የነባር አክሲዮን ዝውውርን መመልከት፣
 4. የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥና ተወያይቶ ማጽደቅ
 5. የኩባንያውን የውጭ ኦዲተሮች ሪፖርት ማዳመጥና ተወያይቶ ማጽደቅ፣
 6. የኩባንያው እ.አ.አ በ2ዐ21/2ዐ22 በጀት ዓመት የተጣራ ትርፍ ክፍፍልን አስመልክቶ በቀረበው

የውሣኔ ሃሳብ ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፣

 1. የውጭ ኦዲተሮችን ሹመት ማጽደቅና አበላቸውን መወሰን፣
 2. የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ የአገልግሎት ክፍያ እና ወርሃዊ አበልን መወሰን፣
 3. የዳይሬክተሮች ቦርድ ዕጩ አባላት ጥቆማና ምርጫ አፈጻጸም መመሪያን ማጽደቅ፣
 4. የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥቆማና አስመራጭ ኮሚቴን የአገልግሎት ክፍያ መወሰን፣
 5. የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥቆማና አስመራጭ ኮሚቴን መምረጥ፣
 6. የጉባዔውን ቃለ ጉባዔ ማጽደቅ፣

ማሳሰቢያ፡-

 • በጉባዔው ላይ በአካል መገኘት የማትችሉ ባለአክሲዮኖች ጉባዔው ከመካሄዱ ከሦስት ቀናት በፊት በኩባንያው ዋና መ/ቤት ወይም በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የኩባንያው ቅርንጫፎች በመገኘት የውክልና ቅጽ በመሙላት በምትወክሉት ወኪል አማካይነት በጉባዔው ላይ መሳተፍና ድምጽ መስጠት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
 • እንዲሁም፣ በጉባዔው ላይ ለመሳተፍና ድምጽ ለመስጠት የሚያስችል ሕጋዊ የውክልና ሥልጣን ዋናውንና አንድ ኮፒ ይዞ በሚቀርብ ወኪል በኩል በጉባዔው መካፈል የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
 • በጉባዔው ላይ በአካል የምትገኙም ሆነ በውክልና የምትሳተፉ ባለአክሲዮኖች ማንነታችሁን የሚያሳይ የታደሰ መታወቂያ ዋናውንና አንድ ኮፒ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እንገልፃለን፡፡

ኦሮሚያ ኢንሹራንስ (አ.ማ.)

የዳይሬክተሮች ቦርድ

አድራሻ፣   ኦሮሚያ ኢንሹራንስ ዋና መ/ቤት፡- ኢትዮ ቻይና መንገድ፣ ድሬዳዋ ሕንፃ አጠገብ

ስልክ ቁጥር ዐ115 57 21 21 / ዐ115 58 81 22