ኦቪድ ኮንስትራክሽን ኃላ/የተ/የግ/ማህ የተለያዩ የግንባታ ስራዎች የስካፎልዲንግ (Scafolding) ማለትም H – Frame System እንዲሁም CHS System ከዚህ በታች በተዘረዘረው መመሪያ መሰረት በግልፅ ጨረታ አወዳደሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ተፈላጊው ምርት ዝርዝር
Overview
- Category : Construction Machinery & Equipment
- Posted Date : 01/23/2023
- Phone Number : 0924574573
- Source : Reporter
- Closing Date : 01/27/2023
Description
ኦቪድ ኮንስትራክሽን ኃላ/የተ/የግ/ማህ
አዲስ አበባ
የስካፎልዲንግ (Scafolding) ግዥ ጨረታ
ድርጅታችን ኦቪድ ኮንስትራክሽን ኃላ/የተ/የግ/ማህ የግንባታ ስራዎችን ከተለያዩ ተቋማት ጋር ውለታ አስሮ እየሰራ ይገኛል። ለነዚህም ለሚያከናውናቸው የተለያዩ የግንባታ ስራዎች የስካፎልዲንግ (Scafolding) ማለትም H – Frame System እንዲሁም CHS System ከዚህ በታች በተዘረዘረው መመሪያ መሰረት በግልፅ ጨረታ አወዳደሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ተፈላጊው ምርት ዝርዝር
Description |
Specification |
Unit |
Quantity Required |
|
1.1 | CHS System | |||
1.11 |
CHS Pipe |
50mm * 3mm and 6m long |
pcs |
49,100 |
1.12 |
Clamp lock Horizontal
Connector |
25cm long |
pcs |
25,300 |
1.13 | Head Jack | 70 cm long | pcs | 21,900 |
1.14 | Base jack | 70 cm long | pcs | 8,800 |
1.15 | 90 degree clamp | pcs | 191,000 | |
1.16 |
Spigot Vertical
Connector |
25 cm long |
pcs |
7,100 |
- ከላይ የተጠቀሱትን ምርቶች ማቅረብ የምትችሉ ተጫራቾች ያላችሁን ማናቸውንም የምርት ዋጋ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በዋናው መ/ቤት ቦሌ ክ/ከ ወረዳ 03 የቤ.ቁ አዲስ ፤ 22 ከጎላጉል ህንጻ ወደ አደይ አበባ እስቴድየም በሚወስደው መንገድ ላይ ወርቁ ህንፃ ጀርባ ኦቪድ ግሩፕ ህንፃ 3ተኛ ፎቅ በሚገኘው የማከላዊ ግዢ ክፍል ቢሮ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዳችሁን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ ባሉት አምስት ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2:30-11:00 ሰአት ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ዘግይቶ የሚቀርብ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
- የጨረታውን አሸናፊዎች ፖስታው በተከፈተ በሁለት ቀናቶች ውስጥ በስልክ በመደወል የምናሳውቅ መሆኑን እየገለጸን አሸናፊዎች ከድርጅታችን ጋር የውል ስምምነት መፈጸም እዳለባቸው ከወዲሁ ለማሳሰብ እንወዳለን።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን የሚያጠቃልል መሆኑን በግልጽ ሁኔታ በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ካልገለጹ በስተቀር ባቀረቡበት ዋጋ ላይ 15 በመቶ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተጨምሮ የሚታሰብ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በሰጡት ዋጋ ላይ የዋጋ ማስተካከያ ወይም ስርዝ ድልዝ ካደረጉ በተስተካከለው ፊት ለፊት መፈረም አለበት ፡፡
- የመጫረቻ ዋጋ በእርሳስ መሙላት አይቻልም፡፡
- አንድ ተጫራች ከአንድ ጊዜ በላይ የጨረታ ሰነድ ማሰገባት አይችልም ፡፡
- በጨረታ ሰነዱ ላይ የተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ ፊርማ ከሌለበት የጨረታው ሰነድ ዋጋ አይኖረውም፡፡
- በጨረታ ሰነድ ላይ ሙሉ አድራሻ ማለትም ስም ፊርማ እንዲሁም ስልክ ቁጥር መፃፍ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ምርት አቅርቦቱ ለህንጻ ግንባታ የሚያስፈልግ በመሆኑ የሚጠበቅበትን የጥራት ደረጃ የሚያሟላ መሆን አለበት፡፡ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለማናቸውም ጥያቄ ከታች በተዘረዘርሩት ስልክ ቁጥሮች በመደወል መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።
092 457 4573
091 136 8165