ኦቪድ ኮንስትራክሽን ኃ/ተ/የግ/ድርጅት የተለያዩ የግንባታ ስራዎችየሰብ ቤዝ (Sub-base material) ፣ (select) ፣ ድንጋይ (stone for hardcore) ፣ ድንጋይ (stone for masonry) የአሸዋ (River sand)፣base coarse ማቴሪያሎችን ከዚህ በታች በተዘረዘረው መመሪያ መሰረት በግልፅ ጨረታ አወዳደሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : Construction Raw Materials
 • Posted Date : 10/29/2022
 • Phone Number : 0911666892
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 11/04/2022

Description

 ኦ ቪድ  ኮን ስት ራክ ሽን  ሃ/የት/የግ /ማ

 አዲ ስ  አ በባ

 የ አሸዋ  ፣ሰሌ ክ ት ፣ የ ሰብ  ቤዝ  አና የ ተለ ያዩ የ መን ገድ  ስራ  ግ ብ ዓቶች  እና  የ ት ራን ስፖር ት   እግ ልግ ሎት   ጨረ ታ

ድርጅታችን ኦቪድ ኮንስትራክሽን ኃ/ተ/የግ/ድርጅት የግንባታ ስራዎችን ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር ውለታ አስሮ እየሰራ ይገኛል። ሆኖም ለሚያከናውናቸው የተለያዩ የግንባታ ስራዎች የሰብ ቤዝ (Sub-base material) ፣ (select) ፣ ድንጋይ (stone for hardcore) ፣ ድንጋይ (stone for masonry) የአሸዋ (River sand)፣base coarse ማቴሪያሎችን ከዚህ በታች በተዘረዘረው መመሪያ መሰረት በግልፅ ጨረታ አወዳደሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

 1. 1. ከላይ የተጠቀሱትን ግብዓቶች ማቅረብ የምትችሉ ተጫራቾች ያላችሁን ማናቸውንም የምርት ዋጋ በሜትር ኩብ ማቅረቢያ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በዋናው መ/ቤት ቦሌ ክ/ከ ወረዳ 03 የቤ.ቁ አዲስ ፤ 22 ከጎላጉል ህንጻ ወደ አደይ አበባ እስቴድየም በሚወስደው መንገድ ላይ ወርቁ ህንፃ ጀርባ ኦቪድ ግሩፕ ህንፃ 3ተኛ ፎቅ በሚገኘው የማከላዊ ግዢ ክፍል ቢሮ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን
 1. 2. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዳችሁን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ ባሉት አምስት ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2:30-11:00 ሰአት ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ዘግይቶ የሚቀርብ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
 2. 3. የጨረታውን አሸናፊዎች ፖስታው በተከፈተ በሁለት ቀናቶች ውስጥ በስልክ በመደወል የምናሳውቅ መሆኑን እየገለጸን አሸናፊዎች ከድርጅታችን ጋር የውል ስምምነት መፈጸም እዳለባቸው ከወዲሁ ለማሳሰብ እንወዳለን።
 1. 4. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን የሚያጠቃልል መሆኑን በግልጽ ሁኔታ በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ካልገለጹ በስተቀር ባቀረቡበት ዋጋ ላይ 15 በመቶ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተጨምሮ የሚታሰብ ይሆናል፡፡
 1. 5. ተጫራቾች በሰጡት ዋጋ ላይ የዋጋ ማስተካከያ ወይም ስርዝ ድልዝ ካደረጉ በተስተካከለው ፊት ለፊት መፈረም አለበት ፡፡
 2. 6. የመጫረቻ ዋጋ በእርሳስ መሙላት አይቻልም፡፡
 3. 7. አንድ ተጫራች ከአንድ ጊዜ በላይ የጨረታ ሰነድ ማሰገባት አይችልም ፡፡
 4. 8. በጨረታ ሰነዱ ላይ የተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ ፊርማ ከሌለበት የጨረታው ሰነድ ዋጋ አይኖረውም፡፡
 5. 9. በጨረታ ሰነድ ላይ ሙሉ አድራሻ ማለትም ስም ፊርማ እንዲሁም ስልክ ቁጥር መፃፍ ይኖርበታል፡፡

10.ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ የአሸዋ አቅርቦቱ ለአርማታ ምርት አልግሎት የሚያስፈልግ በመሆኑ የሚጠበቅበትን የጥራት ደረጃ ሊያሟሉና ከተመረጡ የአሸዋ ክምችት ከሚገኝበት ቦታ መምጣት ያለበት መሆኑ ግንዛቤ ውስት ያስገባ መሆን አለበት፡፡ በተመሳሳይም የሰብ ቤዝ አቅርቦት ዋጋም ይህንኑ መሰረት ያደረገ መሆን ይሆናል፡፡

11.ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለማናቸውም ጥያቄ ከታች በተዘረዘርሩት ስልክ ቁጥሮች በመደወል መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል።

0911666892

0911483102