ከአንበሳ ኢንተርናሽናል  ባንክ  የተሰጠ  መግለጫ

Announcement
Anbesa-International-Bank

Overview

  • Category : Announcement
  • Posted Date : 10/27/2021
  • Phone Number : 000
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 11/05/2021

Description

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየተዘዋወረ ያለው የተሳሳተ መረጃ የባንካችን እውነተኛ ማንነትና ቁመና የማይወክል በመሆኑ የመረጃው ምንጭ የሆኑ አካላት እውነታው ሲገባቸው ይተውታል በሚል እሳቤ ሁኔታውን በዝምታ ስናልፈው ቆይተናል፡፡ ሆኖም ጉዳዩ ከመርገብ ይልቅ እየተባባሰ በመምጣቱ ይህንን አጭርና ተገቢ ምላሽ ለመስጠት ተገደናል፡፡

ሁሉም እንደሚያውቀው አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ቁጥራቸው ወደ 12 ሺህ የሚጠጋ ባለአክስዮኖችና ከሁለት ሚልየን በላይ ደንበኞችን በመያዝ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ የህዝብ ባንክ ነው፡፡ በተጨማሪም ባንኩ በ14 ዓመት እንቅስቃሴው ከ5,500 ለሚበልጡ ቋሚና የኮንትራት ሰራተኞች የስራ ዕድል የፈጠረ ባንክ ነው፡፡ አንበሳ አንተርናሽናል ባንክ የህዝብ ባንክ ነው ስንል በአስር ሺዎች በሚቆጠሩ ባለአክስዮኖች መቋቋሙ ብቻ ሳይሆን፤ በመላ ሀገሪቱ በከፈታቸው ቅርንጫፎች በሚልዮኖች የሚቆጠሩ አስቀማጭ ደንበኞች፣ ተበዳሪዎችና ሌሎች የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚዎችን ይዞ የሚሰራ በሀገሪቱ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ውስጥ ጉልህ አስተዋፅኦ በማበርከት ላይ የሚገኝ በህግ አግባብና በኃላፊነት መንፈስ የሚሰራ የፋይናንስ ተቋም በመሆኑ ጭምር ነው፡፡

ባንኩ ምንም እንኳ በባለአክስዮኖቹ ስብስብ የተመሰረተ ቢሆንም፤ እንደ ፋይናንስ ተቋምነቱ የሀገራችን ህገ- መንግስትና መንግስት የሚያወጣቸውን ህጎች እንዲሁም የብሔራዊ ባንክ መመሪያዎችን ተከትሎ የሚሰራ የፋይናንስ ተቋም ነው፡፡

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና የፋይናንሻል ኢንተለጀንስ ማዕከል የመሳሰሉ ተቆጣጣሪ አካላት ለሚያወጧቸው መመሪያዎች፤ እንዲሁም በፌዴራል ገቢዎች ሚኒስቴር እና በሌሎች የመንግስት ተቋማት ዘንድ ለሚጠበቅበት ሀገራዊ ግዴታ መገዛት ብቻ ሳይሆን፤ የመመሪያዎቹን ተፈጻሚነት በየወቅቱ ለሚያደርጉት የቁጥጥርና ክትትል ስራዎችም ተባባሪ በመሆን በእነዚህ አካላት ዕይታ ስር ሆኖ የሚሰራ ባንክ መሆኑን ለማስገዘብ እንወዳለን፡፡

ስለሆነም ለደንበኞቻችንና ለህዝቡ ግልፅ ማድረግ የምንፈልገው ባንካችን ለህግ፣ ለደንቦችና ለመመሪያዎች ጥሰት ምንም አይነት ቦታ የሌለው መሆኑ ነው፡፡ ከዚህ አኳያ የመንግስትን ህግና መመሪያዎችን ተከታትሎ የማስፈጸም ኃላፊነት የቦርድ እና የማኔጅመንት ብቻ ሳይሆን፤ ሁሉም ሰራተኞች በዕለት ተዕለት ስራቸው የሚተገብሩት ኃላፊነት ነው ብሎ ያምናል፡፡ ለተፈጻሚነቱም ሁሌም ተግቶ ይሰራል፡፡

ማህበራዊ ኃላፊነት ከመወጣት አኳያም በሀገሪቱ ዋና ዋና በሆኑ የልማት አጀንዳዎች ላይ እንደሌሎች አቻ ባንኮች ሁሉ ተሳታፊ ሲሆን፤ ባለፈው ዓመት ብቻ የአንበጣ መከላከል፣ የህዳሴ ግድብ ግንባታ፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ፣ የአዲስ አበባ ተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም እና የገበታ ለሀገር ፕሮግራምን ጨምሮ ለተለያዩ ሀገራዊ ፕሮጄክቶች ማስፈጸምያ ድጋፍ ያደረገ እና ለወደፊትም ግዴታውን ለመወጣት ቁርጠኛ የሆነ ባንክ ነው።

በዚህ አጋጣሚ የፋይናንስ ተቋማትን የመቆጣጠር ኃላፊነት ያላቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና የፋይናንሻል ኢንተለጀንስ እንዲሁም ይመለከተናል የሚሉ ማናቸውም ህጋዊ የመንግስት አካላት ባንኩን በተመለከተ መረጃ ማግኘት ከፈለጉ እስካሁን ስናደርግ እንደነበረው ሁሉ አሁንም በራችንን ክፍት ነው ብቻ ሳይሆን፤ ተገቢውን ምላሽና ማብራሪያ ለመስጠት ሙሉ ፈቃደኛና ተባባሪዎች መሆናችንን ጭምር እየገለጽን ውድ ደንበኞቻችን እና መላው የባንካችን ሰራተኞች እስካሁን ላሳያችሁን ያልተቆጠበ ድጋፍ ልባዊ ምስጋናችንን ማቅረብ እንወዳለን፡፡

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የስኬትዎ አጋ

Send me an email when this category has been updated