ካዲላ ፋርማሲዩቲካልስ (ኢትዮጵያ) ኃ/የተ/የግ/ማ በኦሮሚያ ክልል በፊንፊኔ ልዩ ዞን በገላን ከተማ የሚገኝኝ ሲሆን የጥበቃ አገልግሎት የሚሰጥ ኤጀንሲ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

Cadila-pharmacesticals-logo

Overview

 • Category : Security & Protection Equipment Guarding
 • Posted Date : 01/18/2023
 • Phone Number : 0114671164
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 01/31/2023

Description

የጥበቃ አገልግሎት ለመቅጠር የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ካዲላ ፋርማሲዩቲካልስ (ኢትዮጵያ) ኃ/የተ/የግ/ማ በኦሮሚያ ክልል በፊንፊኔ ልዩ ዞን በገላን ከተማ የሚገኝኝ ሲሆን የጥበቃ አገልግሎት የሚሰጥ ኤጀንሲ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚታሟሉ እና በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶችም ሆነ ግለሰቦች ድርጅቱ የሚገኝበትን ቦታ እና የጥበቃ ቀጠናዎችን ብዛት በአካል ተገኝታችሁ በማየት አገልግሎት ለመስጠት በወር የምትጠይቁትን የክፍያ መጠን ጠቅሳችሁ የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም ሞልታችሁ በማቅረብ በጨረታው እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል፡፡

በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች፡-

 1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሠርተፊኬት (TIN Certificate) የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ (VAT Certificate) እና ጨረታዉን ካሸነፉ ለሚያቀርቡት የጥበቃ አገልግሎት ኢንሹራንስ እና የኢንሹራንስ ሠርተፊኬት ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
 2. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸዉ የጥበቃ ሠራተኞች ሙሉ የአካል ብቃት ያላቸዉ እና በሙሉ ጤንነት ላይ የሚገኙ መሆን አለባቸዉ፡፡
 3. የጨረታዉን ዝርዝር መረጃ ገላን ከተማ ከሚገኘዉ የድርጅቱ ፋብሪካ በአካል ቀርቦ በማየት የቀጠናዎችን ብዛት እና የሚያስፈልገዉን የሰዉ ኃይል እና የደንብ ልብስን ከግምት ዉስጥ ያስገባ የክፍያ መጠን በዝርዝር ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
 4. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ዋጋቸዉን በመሙላት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን እስከ አስረኛዉ ቀን እስከ 6:00 ሰዓት በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
 5. ጨረታዉ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን በአስረኛዉ ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በአዲስ አበባ ቢሮ ይከፈታል፡፡
 6. ተጫራቾች በአዲስ አበባ ከተማ ቋሚ የስራ አድራሻ ሊኖራቸዉ ይገባል፡፡
 7. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል መሰረዝ ይችላል፡፡

አድራሻ፡ፊንፊኔ ዙሪያ ወረዳ ገላን ከተማ ከኖክ ማደያ ከፍ ብሎ ስ.ቁ. 011 445 02 57/58

አዲስ አበባ- ከደንበል ወደ መስቀል ፍላዎር በሚወስደዉ መንገድ ድሪምላይነር ሆቴል ፊት ለፊት     ጥበቡ ሕንጻ 2ኛ ፎቅ

ስ.ቁ 011 467 11 64