ኬር ኢትዮጵያ ልዩ ልዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : Vehicle Sale
 • Posted Date : 03/18/2021
 • Phone Number : 0116183294
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 04/02/2021

Description

ኬር  ኢትዮጵያ ጨረታ ማስታወቂያ

ኬር ኢትዮጵያ መንግስታዊ ያልሆነ የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን ልዩ ልዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ተጫራቾች

 1. ማንኛውም ተጫራቾች የተሸከርካሪዎቹን መለዋወጫ ዝርዝር ዓይነትና ብዛት፣ የጨረታ ሰነድና መመሪያ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ለአንድ ሎት የማይመለስ ብር 200 በድርጅቱ አካውንት ስም ኬር ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ  1000000958976 እየከፈሉ ፡ ኬር ኢትዮጵያ ሀያ ሁለት መንገድ፡ከሌክስ ፕላዛ ጀርባ ወደ አድዋ ድልድይ በሚወስደው መንገድ ሁለተኛ ቅያስ እንዲሁም በአዳማ ኬር ኢትዮጵያ ወደ ሶደሬ መንገድ ጥቁር አባይ ሆቴል ፊት ለፊት ባለው TAF ማደያ አለፍ ብሎ በሚያስገባው የኮብል ስቶን ንጣፍ መንገድ 500 ሜትር ገባ ብሎ ባለው መጋዘን ቢሮ ማስታወቂያው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ መግዛት ይችላሉ፡፡
 2. ተጫራቾች ለሽያጭ የተዘጋጁትን ልዩ ልዩ  የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን በአዳማ ኬር ኢትዮጵያ ወደ ሶደሬ መንገድ ጥቁር አባይ ሆቴል ፊት ለፊት ባለው TAF ማደያ አለፍ ብሎ በሚያስገባው የኮብል ስቶን ንጣፍ መንገድ 500 ሜትር ገባ ብሎ ባለው የመጋዘን ቢሮ ግቢ ውስጥ በመሄድ በስራ ሰዓት ከ3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ መመልከት ይችላሉ፡፡
 3. ተጫራቾች የተሽከርካሪ መለዋዎጫዎችን ዝርዝር የያዘው ሰነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ (Column) ስር የሚገዙበትን ዋጋ በአሃዝና በፊደል ያለ ስርዝ ድልዝ ገልፀው በታሸገ ኤንቬሎፕ /ፖስታ/ በአዲስ አበባ ኬር ኢትዮጵያ ሃያ ሁለት መንገድ ከሌክስ ፕላዛ ጀርባ ወደ አድዋ ድልድይ በሚወስደው መንገድ ሁለተኛ ቅያስ በሚገኘው ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ መጋቢት፡24 ቀን /2013 ዓ.ም 6፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡
 4. የሚሰጡት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጎኑ በተጫራቹ መፈረም አለበት፡፡
 5. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ኤንቬሎፑ ላይ የተጫረቱብትን የመለያ ቁጥር (የኮንትይነር ቁጥር)፡ስማቸውን መፃፍ፣ ፊርማ መፈረምና፣ስልክ ቁጥራቸውን መፃፍ አለባቸው፡፡ 
 6. ጨረታው መጋቢት፡24 ቀን 2013 ዓ.ም በ 6፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 8፡00 ሰዓት ተጫራቾችና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
 7. የጨረታው አሸናፊ የሚሆነው በተሰጣቸው የመለያ ቁጥሮቹ  ለተመደቡት የተሽከርካሪ መለዋዎጫዎች ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ይሆናል፡
 8. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ (20/100) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋጠ ሲፒኦ ከዋና ዋጋ ማቅረቢያው ቅጹ ጋር በፖስታ በማሸግ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ አሸናፊ ለሆኑት የጨረታ ማስከበሪያው በሚከፍሉት ዋጋ ላይ የሚታሰብ ይሆናል፡፡ ለተሸነፉት ተጫራቾች የጨረታ ግምገማ ውጤት ከተገለፀ በኋላ ሲፒኦ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
 9. ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በጨረታው ያሸነፉትን የተሽከርካሪ መለዋዎጫ ዋጋ ከነኮንትይነሩ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት  ውስጥ ከፍለው በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ንብረቱን የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡
 10. ተጫራቾች ስለ አሻሻጡ ዝርዝር ሁኒታ ከጨረታ ሰነድ ጋር ከተያያዘው የተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኝት ይችላሉ፡፡  
 11. ድርጅቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመዘረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0116183294/0923084216 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ኬር ኢትዮጵያ

Send me an email when this category has been updated