ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር ለድርጅታችን አገልግሎት የሚውል ኮምፒዩተር የሚያገለግል አንቲ ቫይረስ,ማይክሮሶፍት ኤስ.ኤስ.ኤል ሰርተፍኬት ግዢ ከላይ የተዘረዘሩትን ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ  አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

Commercial-Nominees-logo-1

Overview

  • Category : Software purch. & Dev. Service
  • Posted Date : 07/16/2021
  • Phone Number : 0115551911
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 08/03/2021

Description

ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ 

 የጨረታ ማስታወቂያ

CN/NCB/16/2013

ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር ለድርጅታችን አገልግሎት የሚውል፡-

ሎት 1:- ለ 200 ኮምፒዩተር የሚያገለግል አንቲ ቫይረስ

ሎት 2:- ማይክሮሶፍት ኤስ.ኤስ.ኤል ሰርተፍኬት ግዢ

ሎት 3:- የኦፊሽያል ፌስ ቡክ ፔጅ ለማሰራት

ከላይ የተዘረዘሩትን ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ  አወዳድሮ በሶስት ዓመት የመአቀፍ ግዢ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡትን ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ እና የዕቃው ዝርዝር መግለጫ በተለየ በሰም በታሸገ ፖስታ እንዲሁም ዕቃዎቹን የምታቀርቡባቸውን ዋጋ በተለየ በሰም በታሸገ ሁለተኛ ፖስታ በማድረግ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

የጨረታ ዶክመንቱን ቦሌ መንገድ ቢትወደድ ባህሩ አብርሀም ህንፃ 4ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል ብር 100.00 በመክፈል ከሰኞ እስከ አርብ (ጠዋት 2፡00-6፡00 እንዲሁም ከሠዓት 7፡00-11፡00) ማግኘት ይቻላል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 20,000 ሲሆን በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. ከመጫረቻ ዶክመንት ጋር መቅረብ ይኖርበታል፡፡

ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንታቸውን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻና የሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ሐምሌ 27 ቀን 2013 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት በ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ያሸነፈው ተጫራች የዕቃዎች ርክክብ የሚደረግበት ቦታ ገርጂ የድርጅቱ ግምጃ ቤት ይሆናል፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያላሟላ ተጫራች ያለተጨማሪ ማስታወቂያ ከውድድሩ ዉጪ ይደረጋል፡፡

ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ

ቦሌ መንገድ ቢትወደድ ባህሩ አብርሀም ህንፃ 4ኛ ፎቅ

ስልክ ቁጥር 011-555 19 11

አዲስ አበባ

ኢትዮጵያ

Send me an email when this category has been updated