ኮከብ አፍሪካ ድንበር ተሻጋሪ ደረጃ 1-ሀ የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ባለንብረቶች ማህበር የ2012-13 የሥራ ዘመን ሂሳብ በጨረታ አወዳድሮ ማስመርመር ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : Auditing Related
 • Posted Date : 08/06/2022
 • Phone Number : 0929907987
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 08/19/2022

Description

ኮከብ አፍሪካ ድንበር ተሻጋሪ ደረጃ 1-ሀ የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ባለንብረቶች ማህበር 

የሂሳብ ምርመራ ሥራ ጨረታ ማስታወቂያ

ማህበሩ የ2012-13 የሥራ ዘመን ሂሳብ በጨረታ አወዳድሮ ማስመርመር ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

 1. በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ምዝገባ ማቅረብ የሚችሉ፤
 2. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤
 3. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፤
 4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 3,000.00 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤
 5. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የማስረከቢያ ጊዜ መጥቀስ አለባቸው፤
 6. ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፤

ስለሆነም በጨረታ ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ በማህበሩ ዋና ጽ/ቤት አ/አ ማረሚያ ቤት አካባቢ ቃሊቲ ሸገር ህንፃ 4ኛ ፎቅ ላይ ቢሮ ቁጥር 408 በመገኘት እንዲያቀርቡ ይጋብዛል፡፡  

ለበለጠ መረጃ የስልክ ቁጥራችን፡-  09 29 90 79 87 እና 09 29 90 79 86