ወጋገን ባንክ አ.ማ. ሲጠቀምባቸው የነበሩ ከዚህ በታች በዝርዝር የተገለፁትን ንብረቶች በዝግ ጨረታ አወዳድሮ    ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Wegagen_bank-logo-reportertenders

Overview

 • Category : Other Sale
 • Posted Date : 09/04/2021
 • Phone Number : 0115548062
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 09/16/2021

Description

ድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር WB/PPA/043/21

ወጋገን ባንክ አ.ማ. ሲጠቀምባቸው የነበሩ ከዚህ በታች በዝርዝር የተገለፁትን ንብረቶች በዝግ ጨረታ አወዳድሮ    ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ሀ.  የኮምፒዩተር ፣ አይቲ እና ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ለ. የቢሮ ማሽኖች እና ሌሎችም መ. ያገለገሉ      የተሽከርካሪ መለዋወጫ

 

ሲስተም ዩኒት፣ ላፕቶፕ፣ሚኒ ኮምፒዩተር፣ኤልሲዲ ሞኒተር፣ሲአርቲ ሞኒተር፣ስዊች፣ ራውተር፣ፓችፓናል፣ራክ፣ ኤዲሲኤል፣ሊንክሳይስ፣ ቴንዳ፣ቲፒ ሊንክ ፣ ዲጂታል ሲግኔቸር፣ዲጂታል ካሜራ እና ፖስ ሎት ሀ- ዩፒኤስ፣ ኤልኪው ኢፕሰን ፕሪንተር ትልቁና ትንሹ፣ተርማል ፕሪንተር፣ሌዘር ጀት ፕሪንተር፣ ታሊ ፕሪንተር፣ ቼክ ስካነር፣ስካነር፣እና ሌሎችም
ሎት ለ- አማርኛ እና እንግሊዝኛ ታይፕራይተር፣ፎቶኮፒ፣ፋክስ፣ኤሌክትሮኒክ ካልኩሌተር፣ዶላርና ዩሮ ዲቴክተር፣የጥበቃ መፈተሻ እና የብር መቁጠሪያ ማሽን እና ሌሎችም
ሎት መ- የተለያየ መጠን ያላቸው ካዝና እና ካሽ ቦክስ

በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች

 1. በጨረታ የሚሸጡት ዕቃዎቹ የሚገኙት የባንኩ ግምጃ ቤት ከሚገኝበት ወደ አቃቂ ፍተሻ ጣቢያ ሲሄዱ ከበላይ አብ ሞተርስ ፊትለፊት ባህሩን መጋዘን ውስጥ ሲሆን እቃዎቹን ከመስከረም 5 እና መስከረም 6 ቀን፣ 2014 ዓ.ም. ከጠዋቱ 300 ሰዓት እስከ ቀኑ 930 ሰዓት ድረስ መመልከት ይችላሉ፡፡
 2. ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበውን ዋጋ ¼ኛ (ሃያ አምስት በመቶ) ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሲፒኦ (CPO) የተጨማሪ እሴት ታክስን 15% (አስራ አምስት በመቶ) በመጨመር ከጨረታው ሰነድ ጋር በታሸገ ኢንቨሎፕ ከነሙሉ አድራሻው እስከ መስከረም 8 ቀን፣ 2014 ዓ.ም 600 ሰዓት ድረስ አዲስ አበባ ስታዲየም ፊትለፊት በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት ወጋገን ህንፃ 16ኛ ፎቅ ግዢና ንብረት አስተዳደር ክፍል ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርበታል፡፡ ያለ ሲፒኦ (CPO) የቀረበ ዋጋ ለውድድር አይቀርብም፡፡ ጨረታው መስከረም 10 ቀን፣2014 ዓ.ም. ከጠዋቱ 400 ሰዓት ይከፈታል፡፡ የጨረታው ሰነድ የባንኩ ዋና መ/ቤት ወጋገን ህንፃ 16ኛ ፎቅ ግዢና ንብረት አስተዳደር ክፍል 00 ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
 3. ማንኛውም ተጫራች በከፊል ወይም በተናጠል መጫረት ይችላል፡፡
 4. የጨረታውን አሸናፊዎች ባንኩ ከአሳወቀበት ቀን ጀምሮ በሶስት ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ሙሉ በሙሉ በመክፈል ንብረቶቹን ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡
 5. የጨረታውነ አሸናፊ ክፍያውን ሙሉ በሙሉ በተባለው ቀን ከፍሎ ንብረቶቹን ያላነሳ ተጫራች ከጨረታው አሸናፊነት ተሰርዞ ለጨረታው ያስያዘው ገንዘብ አይመለስለትም፡፡
 6. በጨረታው አሸናፊ ላልሆኑ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ (CPO) አሸናፊዎች ከተለዩና የሚጠበቅባቸውን ክፍያ ከከፈሉ በኋላ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
 7. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115548062 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ወጋገን ባንክ የብልፅግናዎ አጋር

Send me an email when this category has been updated