ወጋገን ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ከዚህ ቀጥሎ የቀረበውን ንብረት በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Wegagen_bank-logo-reportertenders-1

Overview

 • Category : House & Building Foreclosure
 • Posted Date : 10/19/2022
 • Phone Number : 0115524976
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 11/17/2022

Description

የሐራጅ ማስታወቂያ

  ቁጥር ወጋገን 03/2015

ወጋገን ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ከዚህ ቀጥሎ የቀረበውን ንብረት በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ

ተ.ቁ የተበዳሪው ስም የንብረት አስያዥ ስም አበዳሪው ቅርንጫፍ የንብረቱ አድራሻ የቦታው ስፋት የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ ቁጥር የንብረቱ ዓይነት/የይዞታው አገልግሎት የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር ጨረታው የሚከናወንበት ጊዜ
ከተማ ክ/ከተማ ቀበሌ ቀን ሰዓት
1 ጉጂ ቡና ላኪ ኃ/የተ/የግ/ማህ ግርማ ኤዴማ ባሳዬ ቦሌ ቅርንጫፍ አ.አ ቦሌ 06 388 ካሬ ሜትር ቦሌ/06/34/4805/16522/01 ለመኖሪያ 34,485,736.64 12/03/2015 ዓ./ም ጠዋት

3፡00-6፡00

ማሳሰቢያ

 1. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ (C.P.O) በወጋገን ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት በጨረታው ዕለት በመቅረብና በመመዝገብ በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
 2. የጨረታ አሸናፊ ቀሪውን ገንዘብ በ15 /አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ አጠናቆ መክፈል ይኖርበታል፡፡ ባይከፍል ግን የሐራጁ ውጤት ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፣ ላላሸነፉት ተጫራቾች ግን ያስያዙት ሲፒኦ ይመለስላቸዋል፡፡
 3. የባንኩን የብድር ፖሊሲ እና ፕሮሲጀር የሚጠይቃቸውን መስፈርቶች ለሚያሟላ የጨረታ አሸናፊ ባንኩ የንብረቱን የሐራጅ ጨረታ ዋጋ 25% ድረስ ብድር ሊያመቻች ይችላል፣
 4. ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል፡፡
 5. ጨረታው የሚካሄደው በወጋገን ባንክ ዋና መስሪያ ቤት 9ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ነው፡፡
 6. የምዝገባ ሰዓት ጨረታው በሚካሄድበት እለት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 5፡00 ሰዓት ብቻ ነው፡፡
 7. ለጨረታ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጉብኝት ፕሮግራም ከባንኩ ህግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ይቻላል፡፡
 8. ተበዳሪው/ንብረት አስያዥ በጨረታው ቀንና ሰዓት በቦታው ላይ መገኘት ይችላሉ፤ ነገር ግን ተበዳሪው/ንብረት አስያዥ በጨረታ ቀንና ሰዓት በቦታው ባይገኙ ጨረታው በሌሉበት ይካሄዳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ጨረታው ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች ወይም የተጫራቾች ህጋዊ ተወካዮች ብቻ ናቸው፡፡
 9. ማንኛውንም ለመንግስት ሊከፈል የሚገባውን ክፍያ ሙሉ በሙሉ የሊዝ ክፍያን እና ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ የጨረታ አሸናፊ የሚከፍል ይሆናል፡፡
 • ለበለጠ ማብራሪያ ወይም የጉብኝት ቀጠሮ ለማመቻቸት ወጋገን ባንክ አ.ማ ህግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት 0115-52-49-76 መደወል ይችላሉ፡፡
 • ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡

ወጋገን ባንክ አ.ማ