ወጋገን ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/1992 እና 1147/2011 በ ተሰጠው ስልጣን መሰረት ከዚህ ቀጥሎ የቀረበውን የመኖርያ ቤት ህንፃ እና ተሽከርካሪዎች በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Overview
- Category : House & Building Foreclosure
- Posted Date : 01/02/2023
- Phone Number : 0115524976
- Source : Reporter
- Closing Date : 01/17/2023
Description
ወጋገን ባንክ አ.ማ
ለመጀመርያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ
ቁጥር ወጋገን 10 /2015
ወጋገን ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/1992 እና 1147/2011 በ ተሰጠው ስልጣን መሰረት ከዚህ ቀጥሎ የቀረበውን የመኖርያ ቤት ህንፃ እና ተሽከርካሪዎች በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
ተ.ቁ | የተበዳሪው ስም | የንብረት አስያዥ ስም | አበዳሪው ቅርንጫፍ | የንብረቱ አድራሻ | የቦታው ስፋት | የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ ቁጥር | የንብረቱ ዓይነት/የይዞታው አገልግሎት | የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር | ጨረታው የሚከናወንበት ጊዜ | |||||||||||||||||||||
ክልል | ከተማ | ወረዳ | ቀን | ሰዓት | ||||||||||||||||||||||||||
1 | ማክሼብ ኃላ/የተ/ግል ማህበር
|
የራስወርቅ ታፈሰ
|
ቦሌ
መድኃኔ ዓለም |
አዲስ አበባ | የካ ክ/ከተማ | ወረዳ
05 |
757 ሜትር ካሬ | የካ/208164/10 | መኖሪያ ቤት | 45,114,565.22 | ጥር 24 ቀን 2015 ዓ.ም | 2፡30- 6፡00 ሰዓት | ||||||||||||||||||
ተ.ቁ | የተበዳሪው ስም | የንብረት አስያዥ ስም | አበዳሪው ቅርንጫፍ | የሰሌዳ ቁጥር | የተሸከርካሪው አይነት | የተሰራበት | የሞተር ችሎታ | የነዳጅ አይነት | የጨረታ መነሻ ዋጋ | ጨረታው የሚደረግበት | ||||||||||||||||||||
ፋብሪካ | ሻንሲ ቁጥር | ዘመን | ቀን | ሰዓት | ||||||||||||||||||||||||||
2 | ናኦል
ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር |
የማነ ግርማይ | ተ/ሃይማኖት ቅርንጫፍ | 03-01-96436AA | ያሪስ(አውቶሞቢል) | ጃፓን | VNKKG96330A235066 | 2010 | 996 ሲሲ | ቤንዚን | 700,000.00 | ጥር 09 ቀን 2015 ዓ.ም | 2፡30- 6፡00 ሰዓት | |||||||||||||||||
3
|
ናኦል ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር | የማነ ግርማይ | ተ/ሃይማኖት ቅርንጫፍ | AA-03-A35602 | ፒክአፕ ደብል ጋቤና (አውቶሞቢል) | ቶዮታ ጃፓን | AHTFR29G807047251 | 2015 | 2755 ሲሲ | ነዳጅ | 4,000,000.00 | ጥር 09 ቀን 2015 ዓ.ም | 2፡30- 6፡00 ሰዓት | |||||||||||||||||
ማሳሰቢያ
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ (C.P.O) በወጋገን ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት በጨረታው ዕለት በመቅረብና በመመዝገብ በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ አሸናፊ ቀሪውን ገንዘብ በ15 /አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ አጠናቆ መክፈል ይኖርበታል፡፡ ባይከፍል ግን የሐራጁ ውጤት ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፣ ላላሸነፉት ተጫራቾች ግን ያስያዙት ሲፒኦ ይመለስላቸዋል፡፡
- በጨረታው አሸናፊ ለሆነ፤ የባንኩን የብድር ፖሊሲ፤ መመሪያ እና ቅድመ ሁኔታ ለሚያሟላ በተራ ቁጥር 1 ላይ የተቀመጠውን ንብረት በተመለከተ ጨረታውን ያሸነፈበት ዋጋ 25 በመቶ (25%) ድረስ እንዲሁም በተራ ቁጥር 2 እና 3 ላይ የተዘረዘሩትን ንብረቶቸ በተመለከተእና ሌላ ተጨማሪ መያዣ ንብረት ለሚያቀርብ ተጫራች ጨረታውን ያሸነፈበት ዋጋ 50 በመቶ (50%) ድረስ ባንኩ ብድር ሊያመቻች ይችላል፡፡
- የተጫራቾች የምዝገባ ሰዓት፤ ከጧቱ 2፡30 – 4፡30 ሰዓት ድረስ ብቻ ሲሆን ምዝገባው ከተጠናቀቀ በኋላ ለየአንድ አንዱ ንብረት የተመደበው የጥሪ ሰዓት 30 ደቂቃ ብቻ ነው፡፡ ሆኖም የጨረታው መጠናቀቂያ ሰዓት ድረስ አሸናፊው ካልተለየ አሸናፊ እስኪለይ ድረስ ጨረታው ይቀጥላል፡፡
- በጨረታው የተሻለ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ጨረታውን ካካሄደው ከባንኩ የህግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ሲደርሰው ብቻ አሸናፊ ይባላል፡፡
- ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል፡፡
- ጨረታው የሚካሄደው በወጋገን ባንክ ዋና መስሪያ ቤት 9ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመሰብሰብያ አዳራሽ ውስጥ ነው፡፡
- ለሀራጅ ጨረታ የቀረቡትን ንብረቶች ለመጎብኘት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ከጨረታ ቀን በፊት በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሰው ንብረት ንብረቱ በሚገኝበት አድራሻ በተራ ቁጥር 2 ላይ የተጠቀሰው ተሽከርካሪ ተሽከርካሪው ቆመው በሚገኝበት ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ብሎክ ቁጥር 50 በተለምዶ ቦሌ ሆምስ በሚባለው ግቢ እንዲሁም በተራ ቁጥር 3 ላይ የተጠቀሰው ተሽከርካሪ ንፋስ ስልክ ት/ቤት አጠገብ ያለው ትራንስ የመኪና ማቆሚያ በአካል በመሄድ አልያም የጨረታው ቀን ከመድረሱ ከ7 የሥራ ቀናት በፊት አስቀድሞ ከባንኩ ጋር ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ይቻላል፡፡
- ተበዳሪው/ንብረት አስያዥ/ ወይም ሁለቱም በጨረታው ቀንና ሰዓት በቦታው ላይ መገኘት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ተበዳሪው/ንብረት አስያዡ/ በጨረታ ቀንና ሰዓት በቦታው ባይገኝ ጨረታው በሌለበት ይካሄዳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ጨረታው ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች ወይም የተጫራቾች ህጋዊ ተወካዮች ብቻ ናቸው፡፡
- ማንኛውንም ለመንግስት ሊከፈል የሚገባውን ክፍያ ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ ሙሉ በሙሉ የጨረታው አሸናፊ የሚከፍል ይሆናል፡፡
- ለበለጠ ማብራሪያ ወይም የጉብኝት ቀጠሮ ለማመቻቸት ወጋገን ባንክ አ.ማ ህግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት 0115-52-49-76 መደወል ይችላሉ፡፡
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡
ወጋገን ባንክ አ.ማ