ዋሌት አነስተኛ ፋይናስ ተቋም አ.ማ. የዉጪ ኦዲት ድርጅቶች የማህበሩን ሂሳብ ለቀጣይ ሶስት ዓመታት ማለትም የ2015፣2016፣2017ዓ.ም ኦዲት እንዲያደርጉ ይጋብዛል፡፡

Overview

  • Category : Auditing Related
  • Posted Date : 09/29/2022
  • Phone Number : 0116162777
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 10/12/2022

Description

ዋሌት አነስተኛ ፋይናስ ተቋም አክሲዮን ማህበር

የውጪ ኦዲተር ሥራ ጨረታ

ዋሌት አነስተኛ ፋይናስ ተቋም አ.ማ. በቅርብ ጊዜ ወደ ፋይናንስ ኢንዱስትሪ የተቀላቀለ እና የደንበኞችን ፍላጎት መሰረት ያደረጉ ቀልጣፋ የብድርና ቁጠባ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ ተቋም ነዉ፡፡ ተቋማችን ፍላጎት ያላቸውን የዉጪ ኦዲት ድርጅቶች የማህበሩን ሂሳብ ለቀጣይ ሶስት ዓመታት ማለትም የ2015፣2016፣2017ዓ.ም ኦዲት እንዲያደርጉ ይጋብዛል፡፡ በመሆኑም በውድድሩ የሚሳተፉ ኦዲት ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የታክስ ክሊራንስ፣ የግብር መክፈያ ሰርትፍኬት እና የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን መቅረብ የሚችሉ፣
  2. በኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ ፈቃድ የተሰጠውና የታደሰ ፈቃድ ያለዉና ከምዝገባ ሰርተፊኬት ጋር ማቅረብ የሚችል፤
  3. የአነስተኛ ፋይናስ ተቋማትን በIFRS የተዘጋጀ ሪፖርት ኦዲት በማድረግ ልምድ ያለው፤

ስለሆነም ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ማለትም ከመስከረም 18 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 2 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡00 – 6፡00 እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ7፡00 -10፡00  ድረስ  “ዋሌት አነስተኛ የፋይናስ ተቋም አክሲዮን ማህበር ዋና መስሪያ ቤት ቦሌ መንገድ ጃምፓን ኤምባስ አከባቢ በሚገኘዉ ራንግ ሪል ስቴት ህንፃ 11ኛ ፎቅ በአካል በመገኘት የሚሰሩበትን ዝርዝር ማብራርያና ዋጋ (Technical and Financial Proposal) በማዘጋጀትና ከአስፈላጊ ሰነዶች ጋር በማያያዝ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ዋሌት አነስተኛ ፋይናስ ተቋም ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011-6-16-27-77

ዋሌት አነስተኛ የፋይናስ ተቋም አክሲዮን ማህበር