ዋልታ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኮርፖሬት የ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት ሂሳብ በውጭ ኦዲተሮች ለማስመርመር የኦዲት አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን አወዳድሮ ውል በመያዝ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

Walta-Communications-logo-Reportertenders-2

Overview

 • Category : Auditing Related
 • Posted Date : 04/24/2021
 • Phone Number : 0114670319
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 04/29/2021

Description

የውጭ ኦዲተር አገልግሎት ግዥ ግልፅ ጨረታ

የጨረታ መለያ ቁ.ግ/ጨ/ 043/2013

ዋልታ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኮርፖሬት የ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት ሂሳብ በውጭ ኦዲተሮች ለማስመርመር የኦዲት አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን አወዳድሮ ውል በመያዝ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ተወዳዳሪዎች አስፈላጊ የጨረታ ሰነዶችን በዋናው መስሪያ ቤት የግዥና አቅርቦት ዋና ክፍል በመምጣት የጨረታውን ሰነድ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

በጨረታው የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎች ሊያሟሏቸው የሚገቡ ሰነዶች፡-

 1. ለ2013ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፣
 2. ቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ሰነድ ማቅረብ የሚችሉ፣
 3. የባለሙያዎች ብዛትና የትምህርት ደረጃ መቅረብ ይኖርበታል፣
  • ACCA/CPA/CIA
  • የተፈቀደለት የሂሳብ ባላሙያ(Authorized Accountant)
  • ሌሎች ባለሙያዎች ዝርዝር፣
 1. በዘርፉ(በኦዲቲ) አገልግሎት የዕውቅና ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
 2. የኦዲት ደረጃ የሚገልፅ ሰነድ ማቅረብ የሚችሉ፣
 3. ህጋዊ የብቃት ማረጋገጫ ሰነድ ያላቸው፣
 4. ተመሳሳይ የሚዲያ ተቋማት ጋር መስራታቸውን የሚገልፅ ሰነድ ማቅረብ የሚችሉ እንዲወዳደሩ ይበረታታሉ፣

ጨረታው ሚያዝያ 21/2013 ዓ.ም ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ዋልታ ጨረታውን በሙሉም ይሁን በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ

 • በቅሎ ቤት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ በስተጀርባ
 • ለበለጠ መረጃ ስልክ በስልክ ቁጥር 0114670319 መደወል ይችላሉ

ዋልታ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኮርፖሬት