ዋልታ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኮርፖሬ UPS 60KVA ብዛት አንድ እንዲሁም NewTek Talk show VS 4000 Multi-Channel Video Calling System በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Walta-Communications-logo-Reportertenders

Overview

 • Category : Purchases
 • Posted Date : 11/10/2021
 • Phone Number : 0114670319
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 11/13/2021

Description

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

ዋልታ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኮርፖሬ UPS 60KVA ብዛት አንድ እንዲሁም NewTek Talk show VS 4000 Multi-Channel Video Calling System በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በዘርፉ አቅራቢ የሆናችሁ ድርጅቶች በዚህ ግልፅ ጨረታ እንድትሳተፉ እየጋበዘ፣ ህጋዊ የጨረታ ሰነዱን ዋልታ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኮርፖሬት በሚገኘው የግዥና አቅርቦት ዋና ክፍል የማይመለስ 100.00 ብር በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

በጨረታው የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎች በዋናነት ሊያሟሏቸው የሚገቡ ሰነዶች፡-

 1. ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፣
 2. ቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ሰነድ ማቅረብ የሚችሉ፣
 3. በጨረታ ለመካፈል/ለመሳተፍ የአቅራቢነት ሰርተፊኬት ያላቸው፣
 4. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በሲፒኦ ማስያዝ የሚችሉ ሊሆን ይገባል፡፡

ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ ህዳር 03/2014 ዓ.ም የጨረታውን ሰነድ በመሙላት በዋልታ የግዥና አቅርቦት ዋና ክፍል ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ጨረታው ህዳር 03/2014 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ዋልታ ጨረታውን በሙሉም ይሁን በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ

 • በቅሎ ቤት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ በስተጀርባ
 • ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0114670319 መደወል ይችላሉ፡

ዋልታ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኮርፖሬት