ዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ለእኛ የውሃና መኖሪያ ምህንድስና ክፍል የሥራ ተቋራጮችን፣ አማካሪዎችን እና አቅራቢዎችን ለመምረጥ፣ የተሳትፎ ፍላጎትን መግለጫ (ተፍመ) እንዲያቀርቡ በዚህ ደብዳቤ ይጋብዛል፡፡

Overview

 • Category : Purchases
 • Posted Date : 07/30/2022
 • E-mail : add_purchasing_services@icrc.org
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 08/31/2022

Description

የተሳትፎ ፍላጎትን መግለጫ (ተፍመ) ግብዣ

     ዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ

ኢ-ሜይል፡-     add_purchasing_services@icrc.org

ቀን፡-        July 22/2022 እ.አ.አ.

የተፍመ ቁጥር፡-    WATHAB/ADD22/000XXX

ግብዣው የሚያበቃበት ቀን/ሰዓት፡-    August 31/2022 እ.አ.አ. ቀን 6፡00 ሰዓት እባክዎ፣ ይህንን የተሳትፎ ፍላጎትን መግለጫ (ተፍመ) ጥያቄ መቀበልዎን በኢ-ሜይል ለ add_purchasing_services@icrc.org ያረጋግጡ፡፡

የእርስዎ የተሳትፎ ፍላጎትን መግለጫ ከላይ የተጠቀሰው የተሳትፎ ፍላጎትን መግለጫ የማጣቀሻ ቁጥር ሊኖረውና ወደ ተጠቀሰው አድራሻ ወይም ወደ ኢ-ሜይል አድራሻ   add_purchasing_services@icrc.org  ግብዣው በሚያበቃበት ቀን/ሰዓት ወይም ከዛ ቀድሞ መላክ አለበት፡፡

ከላይ ከተጠቀሰው አድራሻ ወደ ተለየ ሌላ የተሳሳተ አድራሻ የተላከ ሁሉም የተሳትፎ ፍላጎትን መግለጫ እና የዘገየ የተሳትፎ ማቅረቢያ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

ከተጠቀሰው ግብዣው የሚያበቃበት ቀን/ሰዓት በኋላ ገቢ የተደረገ ሁሉም የተሳትፎ ፍላጎትን መግለጫ ለተሳትፎ ብቁ አይደለም፡፡

የተሳትፎ ፍላጎትን መግለጫ ለውጦች ግብዣው ከሚያበቃበት ቀን በፊት በጽሑፍ ሊደርሱ ይገባል፤ የተሳትፎ ማቅረቢያው የተከለሰ መሆኑንም መጠቆም አለባቸው፡፡

ተቀባይነት ያገኘ ሁሉም የተሳትፎ ፍላጎትን መግለጫ በምስጢር ይያዛል፡፡

ሁሉም ተሳታፊ ሻጮች የምርጫ ሂደቱን ውጤት እንደተጠናቀቀ እንዲያውቁ ይደረጋሉ፡፡

አቅራቢውን የመረጠበትን የመጨረሻ የምርጫ ሂደት በተመለከተ ዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ማንኛውንም ማብራሪያ የመስጠት ሃላፊነት የለበትም፡፡

የተሳትፎ ፍላጎትን መግለጫ (ተፍመ)

ዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ (ዓቀኮ)፣ በጦርነት እና በሌሎች የሁከት ሁኔታዎች ለተጎዱ ሰብአዊ ከለላና እርዳታ ለማዳረስ የሚሠራ ዓለምአቀፋዊ፣ ነፃና ገለልተኛ ድርጅት ነው፡፡ ዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ለእኛ የውሃና መኖሪያ ምህንድስና ክፍል የሥራ ተቋራጮችን፣ አማካሪዎችን እና አቅራቢዎችን ለመምረጥ፣ የተሳትፎ ፍላጎትን መግለጫ (ተፍመ) እንዲያቀርቡ በዚህ ደብዳቤ ይጋብዛል፡፡ ዝርዝር ጉዳዮች ከዚህ በታች ቀርበዋል፡፡

 1. የሥራ ውል፣ የማማከር አገልግሎቶችና የዕቃ አቅርቦት

ሀ. ክፍል አንድ፡- የሥራ ተቋራጮች ለሚከተሉት ሥራዎች

የውሃ  ሥራዎች የሥራ ተቋራጭ

የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ እና ማቋቋሚያ የሥራ ተቋራጭ

የኤሌክትሮመካኒካል ሥራ ተቋራጭ

የህንፃ ሥራዎች የሥራ ተቋራጭ

የጠቅላላ ሥራዎች ተቋራጭ

ለ.  ክፍል ሁለት ፡- አማካሪዎች ለሚከተሉት ሥራዎች

የቶፖግራፊ/የመሬት አቀማመጥ ሥራዎች

የሃይድሮጂኦሎጂ ሰርቨይ/የመሬት ላይና የመሬት ውስጥ ውሃ ጥናት ሥራዎች

የኤሌክትሪክ ኃይል ፍላጎት ትንተና የሚሠራ አማካሪ (በኃይል፣ በአካባቢ፣ በአየር ንብረት ለውጥ እና ተያያዥ መስኮች የማማከር አገልግሎት )

በፀሐይ ኃይል ስርዓቶች ልምድ ያለው/ያላት አማካሪ (ጥናቶች፣ ንድፍ ሥራ፣ ስልጠና እና ክትትል)

ንድፍ ሥራዎች

የንጽዕና አጠባበቅን የማስተዋወቅ ሥራ አማካሪ

የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠት ልምድ ያለው/ያላት አማካሪ (በኦፕሬሽን/ሥራ ማሠራት እና ጥገና ለውሃ መገልገያ ኦፕሬተሮች )

አማካሪዎች፡- በኦፕሬሽን/ሥራ ማሠራት እና ጥገና  (በቧንቧ ሥራ፣ ኤሌክትሪክ፣ ህንፃ ግንባታ እና ኤሌክትሮመካኒክ ጉዳዮች)

ሐ. ክፍል ሦስት፡- አቅራቢዎች ለሚከተሉት ዕቃዎች

 • የውሃ ፓምፕ እና ኤሌክትሮመካኒካል ዕቃዎች፡፡ ለምሳሌ፣ የውሃና በቱቦ የሚፈስ እጣቢ ፓምፖች እና ኮንትሮል ፓነሎች (ከላይ የሚደረግ እና በውሃ አካል ውስጥ የሚደረግ፡- መጠኑ ከ5 ኪ. ዋት. እስከ 90 ኪ. ዋት ይደርሳል፡፡)
 • ጀነሬተሮች እና የኤሌክትሪክ ገመዶች፡፡ ይህም ማለት ኮንትሮል ፓነሎችን፣ የማብሪያ ማጥፊያ ቦርዶችን፣ መለዋወጫ ዕቃዎችን እና የኤሌክትሪክ ገመዶችን ያካትታል፡፡ (የተለመደው መጠን ከ45 ኬ.ቪ.ኤ. እስከ 300 ኬ.ቪ.ኤ. ይደርሳል፡፡)
 • የቱቦ ዕቃዎች እና ለተለያዩ የዕቃ ዓይነቶች የሚያገለግሉ ግጣሞች/ፊቲንጎች፡፡ ለምሳሌ፣ ሁሉም የፕላስቲክ እና የብረት ግጣሞች፡- ዩ.ፒ.ቪ.ሲ፣ ፒ.ቪ.ሲ.፣ ኤ.ች.ዲ.ፒ.ኢ፣ ሲ.አይ.፣ ዲ.አይ.…ወዘተ በተለያዩ መጠኖች እና ግጣሞች፣
 • የመጠንና የትግበራ ዓይነቶችን በስፋት የያዙ የፀሐይ ኃይል ስርአቶች (የተሟላ ስርዓት)፡፡ ለምሳሌ፣ ከአነስተኛ እስከ መካከለኛ መጠን ያላቸው፣ ከ1 ኪ. ዋት.  እስከ 10  ኪ. ዋት.  በሆነ መጠን በቢሮዎች፣ በህክምና ማዕከሎች እና ለቤት ውስጥ አገልሎቶች የሚሆኑ፡፡ በተጨማሪም፣ የፀሐይ ኃይልን ለውሃ ፓምፖች ማዋል፣
 • በተለያየ መጠን ውሃን የመያዝ አቅም ያላቸው የውሃ ጋኖች፡፡ ለምሳሌ፣ የፋይበር ጋኖች፣ የተክል ወይም ፓዮኔር ውሃ ጋኖች እና የፕላስቲክ/የፒ.. የውሃ ጋኖች (ከ1 ሜ.ኪውብ. እስከ 15 ሜ.ኪውብ.)
 • የእጅ ፓምፖችን አቅራቢዎች (አፍሪዴቭ እና ኢንዲያማርክ 2)
 • ሪቨርስ ኦስሞሲስ አቅራቢዎች፣ ለምሳሌ፣ ለቤት ውስጥ ከሚሆን መጠን ጀምሮ ለሆስፒታሎች እስከሚውል መካከለኛ መጠን ድረስ
 • የማብሰያ እንስራዎች እና የተሻሻሉ ሮኬት ምድጃዎች (አይ.አር.ኤስ.) አቅራቢዎች
 • ዳቦ መጋገሪያ ምድጃ፣ ሊጥ መቀላቀያ ማሽን፣ የእንጀራ ዱቄት መንፊያ ማሽን፣ የእህል መፍጫ ማሽን አቅራቢዎች
 • ብርድልብስ እና ፍራሽ አቅራቢዎች
 1. የሚጠበቁ አቅራቢዎችን ለመምረጥ የቀረቡ የቅድመብቃት መለያ መስፈርቶች

በሚከተሉት ነጥቦች ውስጥ ዝርዝር የብቃት መስፈርቶች ተተንትነዋል፡፡ ቅድመሁኔታዎቹን የሚያሟሉና ፍላጎቱ ያላቸው አካላት ብቻ ማመልከት ያስፈልጋቸዋል፡፡

ሀ.  አመልካቹ/ቿ አስፈላጊ የሆኑ ህጋዊ ሰነዶች እና ዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በሚሠራባ በአገሪቱ ውስጥ በሚገኝ ሩቅ ቦታበፈታኝ ሁኔታዎች ውስጥ ለመሥራት ፍላጎት ሊኖር/ሊኖሯት    ይገባል፡፡   ለ. አመልካቹ/ቿ ባለፉት ሦስት የበጀት ዓመታት ውስጥ  በቀጥታ ለተገልጋይ/ለተጠቃሚዎች ተገቢ ዕቃዎችን ቢያንስ በዝቅተኛ መጠን በማቅረብ የሥራ ልምድ ሊኖረው/ሊኖራት ያስፈልጋል፡፡ የቤት ውስጥ አቅርቦቶችን በተመለከተ፣ አመልካቹ/ቿ የተረጋገጡ የግዥ ትዕዛዝ ቅጂዎችን እና ከዋንኛ ተጠቃሚዎች የተገኙ ዋንኛ የአፈጻጸም ምስክር ወረቀቶችን ለማስረጃዎቹ/ቿ ድጋፍ እንዲሆኑ ማቅረብ ይገባዋል/ይገባታል፡፡

መ. ማናቸውንም የመብት ክፍያዎችን፣ ወጪና ኪሣራን፣ የፍርድ ቤት ችሎት ወጪን…ወዘተ፣ ከውጭ  አገር የዕቃ ገዥ ከሆነ አካል ወይም ከዚህ የተሳትፎ ፍላጎትን መግለጫ ከሚመነጭ ወይም ከየተሳትፎ  ፍላጎትን መግለጫው ጋር ከሚገናኝ ከስምምነቶቹና ከቅድመሁኔታዎቹ ከማንኛውም ጉዳይ ጋር  የሚያያዝ ዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴን የሚመለከት የዕዳ ክፍያን ሁልጊዜ አመልካቹ/ቿ   ይከፍላል፡፡

ሠ.  አመልካቹ/ቿ በማንኛውም መንግስት ወይም የመንግስት ድርጅት የቅጣት መዝገብ ውስጥእንደማይገኝ፣ የተከለከለ ወይም የታገደ እንዳልሆነ፣ በውሉ ዕለት በጽሑፍ የቀረበ የመሀላ ቃል ገቢ ያደርጋል፡፡ በጽሑፍ የቀረበ የመሀላ ቃል በሚገባ ማኅተም ይደረግበታል፤ ማረጋገጫ ፊርማም ይፈረምበታል፡፡

ረ. አቅራቢዎች በሁሉም የዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ጠቅላላ የቅድመ ሁኔታ አንቀጾች፣      እንደየትግበራቸው ሁኔታ እንዲተገበሩ  ይስማማሉ፡፡

 1. የሥራ ወሰን፡-

ሀ) የተመረጡት አመልካቾች የዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ፓናል/ቡድን አካል ይመሰርታሉ፤ ይህም የዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ አቅራቢዎች አካል ሆኖ የሚሠራ ይሆናል፡፡ ዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ የአቅርቦት ውሎችን ዘወትር ከአቅራቢዎቹ ፓናል/ቡድን ጋር በመሆን ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡ አቅራቢዎቹ በውሉ በተጠቀሱት የምርት ብቃት መግለጫ ጉዳዮችና ምርትን የማስረከቢያ መስፈርቶችን አጥብቀው በማክበር መሥራት ይጠበቅባቸዋል፡፡

ለ) አቅራቢው ሲፒኦ/ውልን በአግባቡ ለመፈጸሙ የሚቀርብና ለውል በውል አግባብ በዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ዋጋው የሚወሰን የገንዘብ ዋስትና ገቢ ማድረግ የሚኖርበት ሊሆን ይችላል፡፡

ሐ) በውሉ የሚካተቱ የክፍያ ሁኔታዎች፣ ነጥብ በነጥብ እየታዩ በዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ እና በአቅራቢው/ዋ መካከል በሚደረግ ድርድር የሚታዩ ይሆናሉ፡፡

መ) የተመረጠው/ችው አቅራቢ ከላይ ከተጠቀሱት ከማናቸውም ወይም ከሁሉም ተግባሮች ጋር የሚገናኙ ሁሉም የመንግስት ህግ፣ ፖሊሲዎች፣ መመሪያዎች፣ ትዕዛዞች…ወዘተ መከበራቸውን ማረጋገጥ ይኖርበታል/ይኖርባታል፡፡

ሠ) የተመረጠው/ችው አቅራቢ ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚወጡ የኢትዮጵያ መንግስትን የህግ ነክ ቅድመሁኔታዎችንና መመሪያዎችን ለማክበር መስማማቱን ለመግለጽ ይፈርማል፤ ሃላፊነትም መውሰድ አለበት/አለባት፡፡

 1. የውል ማዕቀፎችና ቅድመ ሁኔታዎች፡-

ሀ) አመልካቹ/ችዋ፣ በፓናል ውስጥ ምዝገባ በሚደረግበት ቀን፣ በኢትዮጵያ ወይም ከኢትዮጵያ ውጭ የተጠቀሰውን አገልግሎት ማቅረብ እንዳይችል/እንዳትችል፣ በማንኛውም መስተዳደር (ማዕከል ወይም መንግስት)/የመንግስት ዘርፍ ድርጅት፣ ቢዝነስ ከመሥራትና በጨረታዎች ከመሳተፍ መከልከል፣ መታገድ ወይም በቅጣት መዝገብ ውስጥ መጠቀስ ሊፈጸምበት/ባት አይገባም፡፡ ሀሰተኛ ሰነድ ገቢ ሆኖ ሲገኝ (በማንኛውም ወቅት)፣ እንደዛ ያለ/ያለች አቅራቢ ውድቅ ይደረጋል/ትደረጋለች፡፡

ለ)  በዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ብቻ በሚደረግ ነፃ ውሳኔ መሰረት አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ፣ አመልካቹ/ችዋ ገቢ ያደረጋቸውን/ያደረገቻችውን ሰነዶችን ከማረጋገጥ ሥራ ጋር ተያይዞ፣ አመልካቹ/ችዋ ተጨማሪ መረጃ/ማረጋገጫ እንዲያቀርብ/እንድታቀርብ ሊጠየቅ/ልትጠየቅ ይችላል/ትችላለች፡፡

ሐ) ለዚህ “የተሳትፎ ፍላጎትን መግለጫ” ምላሽ ለመስጠት ሲባል ገቢ የተደረጉ ሁሉም ሰነዶች ገቢ ሲደረጉ የዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ንብረት ይሆናሉ፤ በጥብቅ ምስጢራዊነትም የሚያዙ    ይሆናሉ፡፡

መ) ተመሳሳይ አድራሻ ወይም የመገኛ ዝርዝር መረጃዎች ያሏቸው አመልካቾች ተቀባይነት የላቸውም፡፡.

ሠ) ለዚህ የተሳትፎ ፍላጎትን መግለጫ ለሚያመለክት ለማንኛውም አመልካች፣ ዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በውል ወይም በሌላ በማንኛውም መንገድ የታሠረ አይደለም፡፡ በወደፊት ሁኔታዎች ውስጥ፣ በሃሳብ መልክ የሚቀርቡ ጽንሰሃሳቦችን ማካተትን ጨምሮ፣ ዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ የተሳትፎ ፍላጎትን መግለጫውን ካቋረጠ፣ ከለወጠ ወይም ሂደቱን ለተወሰነ ጊዜ ካገደ ወይም በዚህ የተሳትፎ ፍላጎትን መግለጫ ስር የተፈቀደ ሌላ እርምጃ ከወሰደ፣ አመልካቾች ከሚያቀርቡት ከዚህ የተሳትፎ ፍላጎትን መግለጫ ጋር ተያይዞ፣ ለማናቸውም ወጪዎች ወይም ለካሣ ዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ተጠያቂ አይሆንም፡፡ የየተሳትፎ ፍላጎትን መግለጫው ጥያቄ በዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ እና በአቅራቢው/ዋ ወይም አቅራቢ ሊሆን በሚችል አካል መካከል የሚከሰት የማንኛውም ሂደት፣ ውል ወይም የውል ግዴታዎች  ጥገኛ አይደለም፡፡

ረ) ከላይ የተጠቀሱት የውል ማዕቀፎችና ቅድመ ሁኔታዎች ሙሉ በሙሉ በአመልካቹ/ችዋ ታሳቢ መደረግ ይኖርባቸዋል፡፡ ከላይ ከተጠቀሱት ቅድመሁኔታዎች ጋር የማይስማማና ያልተሟሉ ሰነዶችን የያዘ የቅድመብቃት ጨረታ ወዲያው ውድቅ ይደረጋል፡፡

ሰ) ዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ የማንኛውንም የተሳትፎ ፍላጎትን መግለጫ አቅርቦት፣ ምንም ዓይነት ምክንያት ሳይሰጥ የመቀበል ወይም ያለመቀበል መብት አለው፡፡ ይህን በተመለከተ፣ የዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ውሳኔ፣ ለሁሉም ተሳታፊ አቅራቢዎች፣ የመጨረሻና አሣሪ ይሆናል፡፡

ሸ) የአቅራቢዎች በዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በፓናል ውስጥ እንዲመዘገቡ መደረግ፣ ምዝገባው ዋጋ በሚኖረው ጊዜ ውስጥ ዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ውሎችን እንዲፈጽም የሚያደርግ ምንም ዓይነት የዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴን ግዴታን አያስከትልም፡፡ ለሚጠበቁ ተጫራቾች በቅድሚያ የተሰጠ ማስታወቂያ ሳይኖር፣ ዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ የሂደቱን ከፊል ወይም ሙሉ ክፍል የመተው መብቱ አለው

 1. የሚፈለጉ ሰነዶች፡-

የብቃት መስፈርቶች

ፍላጎቱ ያላቸው ኩባንያዎች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን የብቃት መስፈርቶችን ካሟሉ ብቻ እንዲያመለክቱ ይበረታታሉ፡፡ መረጃቸውንም (አስፈላጊ በሆነበት ቦታ) በተዘረዘሩት የብቃት መስፈርቶች መሰረት ገቢ እንዲያደርጉ ይፈለጋሉ፡፡

የብቃት መስፈርቶች

 

ገቢ የሚደረግ መረጃ ዝርዝር ጉዳዮች/የሚፈለግ መረጃ
ደረጃ እባክዎ፣ የድጋፍ ሰነድዎን ጨምረው፣ እርስዎ በየትኛው ክፍል ወይም ደረጃ ላይ እንዳሉ ይግለጹ
ቢያንስ የሁለት ዓመት ልምድ በግንባታ ወይም በማማከር አገልግሎቶች ቢያንስ የሁለት ዓመት ልምድ ማስረጃ
ስልጣን ባላቸው አካላት ተፈጻሚ በሚሆንበት ሁኔታ ተገቢ ምዝገባ

 

ተገቢ የኩባንያ ምዝገባ ስለመካሄዱ ማስረጃ
 የኩባንያ ግለታሪክ መግለጫ፡- ቢያንስ ዝቅተኛ የሙያ ዕውቀትን፣ የልምድ ዓመታትንና የባለቤትነት ዝርዝር መረጃዎችን የሚያመለክት · የሰራተኞችን ብዛት፣ ዋንኛ የሙያዊ ችሎታ መስኮችንና ልምድን፣ በቢዝነስ የቆየበትን ዓመታት ብዛት የሚያሳይ የኩባንያው ግለታሪክ መግለጫ

· የሰራተኞችን አቅም፣ አሁን የሚገኙ ሃብቶችን፣ የውክልና እና የባለቤትነት መረጃ ጥቆማን ማካተት

· በፆታዊ ትንኮሳ ጉዳይ ላይ የተዘጋጀ የኩባንያው ፖሊሲ

· በህፃናት ሥራ ጉዳይ ላይ የተዘጋጀ የኩባንያው ፖሊሲ

· በፆታ ጉዳይ ላይ የተዘጋጀ የኩባንያው ፖሊሲ (የወንድ ለሴት ተቀጣሪዎችን ምጣኔ ይግለጹ፡፡)

· በእርሻ ዕቃዎች መስክ ቢያንስ ሁለት ዓመት ልምድ ያላቸው ኩባንያዎች ብቻ ታሳቢ የሚደረጉ መሆኑን ያስተውሉ፡፡

 

ታክስ የተደረገ ገቢ ዝርዝር

 

 

ባለፉት ሦስት የበጀት ወራት ውስጥ በመዝገብ የተያዘ፤ ማለትም ከጥር እስከ መጋቢት/2022 እ.አ.አ. የተደራጀ፣ የገቢ ግብር ዝርዝር መረጃ ቅጂ መቅረብ አለበት

ከበጀት አንጻር ዘላቂ ቢያንስ የሦስት ዓመት የበጀት አጠቃቀም መግለጫዎች/ከ2019 እ.አ.አ. እስከ 2021 እ.አ.አ. የተሠሩ የኦዲት ሪፖርቶች ወይም የባንክ ሂሳብ መግለጫዎች

ያስተውሉ፡- ለግምገማ ዓላማችን ስኬት መሰረታዊና የግዴታ መረጃ የሆኑትን መስፈርቶቹን ለማጠቃለል፣ እባክዎ፣ የሚከተሉትን ነጥቦች በጥንቃቄ ለመሙላት ሞክሩ፡፡ ይህ ካልተሟላ፣ የመለየት ሥራ ሲሠራ፣ የመጀመሪያው ውድቅ ማድረጊያ ጉዳይ ሊሆን ይችላል፡፡  

 (1) የሙያዊ ችሎታ ደረጃ፣ በተመሳሳይ ፕሮጀክቶች የነበረ ልምድ እና ለተፈላጊ መሳሪያዎች ባለቤትነት ማረጋገጫ የሚሆኑ የምስክር ወረቀቶች፤ (2) የበጀት መረጃ፡-ባለፉት ተከታታይ ዓመታት (ለየብቻ) የተመዘገበ ከሽያጭ የተገኘ ገንዘብ መጠን በፐርሰንት፤ (3) ከርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ጋር የነበረ ልምድ፤ ዋንኛ ደንበኞችዎንም ይጥቀሱ፡- እባክዎ፣ ከዓለም አቀፍ ተቋማት፣ ከተባበሩት መንግስታት፣ መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች እና ከዋንኛ ደንበኞች ጋር የተፈጸሙ የቅርብ ጊዜ ውሎችን ሪፖርት ያድርጉ፤ (4) የቅርብ ጊዜ የቫት መግለጫ ቅጂ እና ለተገቢው የጉሙሩክ ባለስልጣን ቅርንጫፍ ቢሮ የተጻፈ የክፍያ ፋክቱር

            6) የተሳትፎ ፍላጎት መግለጫን ገቢ ማድረግ

ፍላጎቱ ያላቸው አመልካቾች ማመልከቻዎቻቸውን ቀደም ብለው ነገር ግን የተሳትፎ ፍላጎት መግለጫው ገቢ ከሚደረግበት ከመጨረሻው ቀንና ሰዓት ማለትም August 31.2022 እ.አ.አ. ሳያሳልፉ ገቢ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡

ሀ) የተሳትፎ ፍላጎትን መግለጫው ገቢ የሚደረግበት ቦታና ገቢ የሚደረግበት ዘዴ፡-

የተሳትፎ ፍላጎት መግለጫው በፍጥነት ፖስታ ቤት፣ ኢ-ሜይል ወይም በእጅ በኩል ለሎጂስቲክ ክፍል ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ መላክ አለበት፡፡

ለግዥ ክፍል ኃላፊ

ADD የሎጅስቲክ ክፍል

ዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ (ዓቀኮ)

ቦሌ ክፍለከተማ፣ ቀበሌ 13፣ አዲስ አበባ ወይም ለ፡-

add_purchasing_services@icrc.org

ለ) በፋክስ ተልከው የደረሱ ማመልከቻዎች ተቀባይነት የላቸውም፡፡

ሐ) ዘግይቶ የደረሰ የተሳትፎ ፍላጎትን መግለጫ ፡- ማንኛውም ከትክክለኛው ቀንና ሰዓት በኋላ ለዓለም

አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ የደረሰ የተሳትፎ ፍላጎትን መግለጫ ወዲያው  ውድቅ ደረጋል፡፡

መ) ግብዣው ከሚያበቃበት ቀን በኋላ የሚመጣ ማንኛውም የማብራሪያ ጥያቄ ተቀባይነት የለውም፡፡

 • ማሳሰብያ

የዚህ ሰነድ ጉዳይ በማናቸውም መንገድ ዓቀኮን ሁሉንም ወይም ማንኛውንም የቅድመብቃት የፓናል ውስጥ የመመዝገብ ሂደት ወደፊት እንዲቀጥል ግዴታ አይጥልበትም ወይም በሌላ መልኩ አያስገድደውም፡፡ ለድርጊቱ ደጋፊዎች ወይም ደጋፊ እንደሚሆኑ ለሚታሰቡ አካላት ቀደም ብሎ ማስታወቂያ ሳይሰጥ፣ ዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ፣ በራሱ ፍጹም ነፃ ውሳኔ፣ አጭር ዝርዝር ሊያወጣ፣ ሊቀበል፣ ውድቅ ሊያደርግ ወይም ለመተው ምርጫ ሊያደርግ ወይም ሂደቱን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት ላይሰጠው ይችላል፡፡ ዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ፣ የተሳትፎ ፍላጎትን መግለጫውን ሙሉ በሙሉ፣ ምንም ምክንያት ሳይሰጥ፣ በማንኛውም ጊዜ የመሰረዝ መብት አለው፡፡ በዚህ የተሳትፎ ፍላጎትን መግለጫ የቀረቡት መረጃዎች ታማኝ ሆነው ይፋ ተደርገዋል፡፡

ተጨማሪ መረጃ እና/ወይም ማብራሪያ ከፈለጉ፣ እባክዎ፣ እኛን ለማግኘት ወደ ኋላ አይበሉ፡፡

ዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ

የግዥ ቡድን