ዓባይ ኢንሹራንስ አ.ማ 11ኛ መደበኛ እና 11ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባዔ የስብሰባ ጥሪ

Announcement
Abay-Insurance-Logo-Reporter-Tenders

Overview

 • Category : Announcement
 • Posted Date : 11/08/2021
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 12/12/2021

Description

 ዓባይ ኢንሹራንስ አ.ማ

11ኛ መደበኛ እና 11ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባዔ የስብሰባ ጥሪ

ዓባይ ኢንሹራንስ አ.ማ ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የንግድ ምዝገባ ቁጥር MT/AA/2/0011521/2004 ፈቃድ አውጥቷል፡፡ ዋና መ/ቤቱም አዲስ አበባ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 03 አትላስ አካባቢ በሚገኘው የአክሲዮን ማህበሩ ህንፃ የሚገኝ ሲሆን የማህበሩ ዋና ገንዘብ ብር 300,000,000 ደርሷል፡፡

አክሲዮን ማህበሩ የባለአክሲዮኖች 11ኛ መደበኛ እና 11ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባዔ ቅዳሜ ታህሳስ 2 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በአዲስ አበባ ፒያሳ አካባቢ በሚገኘው ግራንድ ኤልያና ሆቴል የስብሰባ አዳራሽ ጉባዔውን የሚያካሂድ በመሆኑ የኩባንያው ባለአክስዮን የሆናችሁ ማንነታችሁን የሚገልጽ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፣ መንጃ ፈቃድ ወይም ፓስፖርት ዋናውን እና ኮፒ በመያዝ በተጠቀሰው ቦታ፣ ቀንና ሰዓት በስብሰባው ላይ እንድትገኙ ጥሪያችንን እያስተላለፍን የእለቱ የመወያያ አጀንዳዎች ከዚህ የሚከተሉት መሆናቸውን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡

የ11ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች

 1. የጉባዔውን ድምፅ ቆጣሪዎች መሰየም
 2. ምልዓተ ጉባዔ መሟላቱን ማረጋገጥ
 3. የጉባዔውን አጀንዳ ማፅደቅ
 4. አዳዲስ የአክሲዮን ሽያጭ እና አክሲዮን ዝውውሮችን ማፅደቅ
 5. እ.ኤ.አ የ2020/21 የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርት ተወያይቶ ማፅደቅ
 6. እ.ኤ.አ የ2020/21 የውጭ ኦዲተሮችን ዓመታዊ ሪፖርት ተወያይቶ ማፅደቅ
 7. የውጭ ኦዲተሮችን ሹመት ማፅደቅ እና የአገልግሎት ክፍያቸውን መወሰን
 8. የባለአክሲዮኖችን የ2020/21 የትርፍ ድርሻ ክፍፍል መወሰን
 9. የዳይሬክተሮች ቦርድ የ2020/21 ዓመታዊ የአገልግሎት ክፍያን መወሰን
 10. የዳይሬክተሮች ቦርድ ምልመላና አስመራጭ ኮሚቴ ምርጫ ማካሄድ እና አበላቸውን መወሰን
 11. ቃለ-ጉባዔ ማፅደቅ

የ11ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች

 1. ድምፅ ቆጣሪዎችን መሰየም
 2. የጉባዔው ምልዓተ ጉባዔ መሟላቱን ማረጋገጥ
 3. የጉባዔውን አጀንዳ ማፅደቅ
 4. የኩባንያውን ካፒታል ማሳደግ እና አፈፃፀሙ ላይ ውሳኔ ማሳለፍ
 5. የዳይሬክተሮች ቦርድ ምልመላና አስመራጭ ኮሚቴ የምርጫ ማስፈፀሚያ መመሪያን ማፅደቅ
 6. ቃለ-ጉባዔ ማፅደቅ

ማሳሰቢያ

በጉባዔው ላይ በአካል መገኘት የማትችሉ ባለአክሲዮኖች ጉባዔው ከሚካሄድበት ከሶስት የስራ ቀናት በፊት በኩባንያው ዋና መ/ቤት ወይም አቅራቢያዎ በሚገኝ ቅርንጫፋችን በመቅረብ የውክልና ፎርም መሙላት ወይም ውል ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠው አካል ፊት ስብሰባው ላይ ለመገኘትና ድምፅ ለመስጠት የሚያስችል የውክልና ሰነድ ዋናውን እና አንድ ቅጅ ከተወካዩ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ዋናውን እና ኮፒ ይዞ በመቅረብ በጉባዔው ላይ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃን፡፡

የዓባይ ኢንሹራንስ አ.ማ

የዳይሬክተሮች ቦርድ