ዓባይ ኢንሹራንስ አ.ማ. ለዋናዉ መ/ቤት ህንፃ እና በተለያዩ አደጋ ለደረሰባቸዉ ተሸከርካሪዎች ማቆያ ቦታ የጥበቃ አገልግሎት ለማግኘት በመስኩ የስራ ፈቃድ ያላቸዉን ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ አገልግሎት ለማግኘት ይፈልጋል።

Abay-Insurance-Logo-Reporter-Tenders

Overview

 • Category : Security & Protection Equipment Guarding
 • Posted Date : 05/20/2021
 • Phone Number : 0115535808
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 06/07/2021

Description

ዓባይ ኢንሹራንስ አ.ማ.

የጥበቃ ስራ አገልግሎት ለማግኘት የወጣ ጨረታ

  የጨረታ ቁጥር  ዓኢ /007/2013

ዓባይ ኢንሹራንስ አ.ማ. ለዋናዉ መ/ቤት ህንፃ እና በተለያዩ የትራፊክ አደጋ ምክንያት አደጋ ለደረሰባቸዉ ተሸከርካሪዎች ማቆያ ቦታ የጥበቃ አገልግሎት ለማግኘት በመስኩ የስራ ፈቃድ ያላቸዉን ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ አገልግሎት ለማግኘት ይፈልጋል። በመሆኑም በዘርፉ ህጋዊ የስራ ፈቃድ ያላችሁ ድርጅቶች በጨረታዉ እንድትሳተፉ  እንጋብዛለን።

ተጫራቾች  ማሟላት  ያለባቸዉ  ነገሮች

 1. በመስኩ የታደሰ ህጋዊ የሥራ ፈቃድ ያላቸው፣ በሚመለከተው መ/ቤት የተመዘገቡበት የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ ከፖሊስ  የተሰጠ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ያላቸው እና በመስኩ ያላቸውን የስራ ልምድ ማስረጃ እንዲሁም ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ እና  የግብር መለያ ቁጥርና ተያያዥ ሰነዶች ማቅረብ አለባቸዉ።
 2. ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡ እነዚህ ሰነዶች በቴክኒካል ኘሮፖዛል ፖስታ ውስጥ ታሽገው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 3. ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ሰነድ ከነመመሪያው የማይመለስ ብር 100 (መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከኩባንያው ዋና መ/ቤት 4ኛ ፎቅ ሃብት አስተዳደር ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
 4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና ይሆን ዘንድ የጨረታውን 2 በመቶ (2%) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ(CPO) ወይም የባንክ ዋስትና ማረጋገጫ ደብዳቤ  (Bank Guarantee)  ፖስታ ውስጥ በፖስታ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
 5. ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሃሳባቸውን (ቴክኒካል ሰነድ) ዋና እና ኮፒ እንዲሁም  ፋይናንሻል ዋና እና ኮፒ  በማዘጋጀት  በግልፅ ከፋፍለው በተለያየ ፖስታ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 6. ጨረታው ግንቦት 16 ቀን 2013 ዓ.ም እሰከ ግንቦት 30 ቀን 2013  ከቀኑ 8፡00 ድረስ ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በእለቱ ግንቦት 30 ከሰዓት 8፡30  ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻዉ በተገኙበት  ይከፈታል፡፡ 
 7. አሸናፊው ተጫራች ከኩባንያው ጋር የስራ አፈፃፀም ውል ይዋዋላል፡፡
 8. ኩባንያው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 9. ለተጨማሪ ማብራርያ በስልክ ቁጥር 251-11-5-53 58 08 ወይም 011-6-72-50-09 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡                                  

አድራሻ፡      ዓባይ ኢንሹራንስ አ.ማ.

 ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 03 የቤት ቁጥር 377 አትላስ ሆቴል አካባቢ

ሀብት አስተዳደር መምሪያ 4ኛ ፎቅ 405 ቢሮ ቁጥር

        ስልክ:- 251-6-72-50-09 (251-11-5-53-58-08)

         ፖ.ሳ.ቁ.  5879  አዲስ   አበባ  ኢትዮጵያ

Send me an email when this category has been updated