ዓባይ ኢንሹራንስ አ.ማ የካሳ ክፍያ ፈፅሞ የተረከባቸውን ከባድና ቀላል የተጎዱ ተሽከርካሪዎች፤ልዩ ልዩ የተሸከርካሪ ውጫዊና ውስጣዊ አካላት ቅሪቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::

Abay-Insurance-Logo-Reporter-Tenders-1

Overview

 • Category : Spare Parts Sale & Supply
 • Posted Date : 05/27/2021
 • Phone Number : 0115154507
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 06/11/2021

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ዓባይ ኢንሹራንስ አ.ማ

Abay Insurance S.C

 1. ዓባይ ኢንሹራንስ አ.ማ የካሳ ክፍያ ፈፅሞ የተረከባቸውን ከባድና ቀላል የተጎዱ ተሽከርካሪዎች፤ልዩ ልዩ የተሸከርካሪ ውጫዊና ውስጣዊ አካላት ቅሪቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
 2. ተሸከርካሪዎቹን ፤ ውጫዊና ውስጣዊ አካላት ቅሪቶችን ለመግዛት በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ሁሉ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ከሃናማርያም አደባባይ ወደ ቃሊቲ በሚወስደው ቀለበት መንገድ 800 ሜትር ወረድ ብሎ በሚገኘው የኩባንያው ሪከቨሪ  በመቅረብ  ከግንቦት 23 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ ሰኔ 4 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ባሉት የስራ ቀናት በስራ ሰዓት ብቻ በመምጣት ማየት ይቻላል ::
 3. ተጫራቾች ተሽከርካሪውን ወይም እቃዎቹን የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ከግንቦት 23  ቀን 2013 ዓ.ም እስከ ሰኔ 05 ቀን 2013 ዓ.ም ከጧቱ 3.00 ሰዓት ድረስ አትላሰ አካባቢ በሚገኘው የአባይ ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የሚጫረቱበትን ዕቃ ኮድ በጨረታው ፖስታ ላይ በመጻፍ የሚወዳደሩበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ::
 4. ተጫራቾች ዝቅተኛ ማስያዣ ብር 1,000 ሆኖ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 15% በ CPO የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል:: በጨረታው ለተሸነፉ ተወዳዳሪዎች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታው ከተከፈተበት ሶስት የስራ ቀናት በኃላ ተመላሽ የሚደረግ ይሆናል::
 5. የጨረታው አሸናፊዎች የተሸከርካሪዎችንም ሆነ የዕቃዎችን ዋጋ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ በመክፈል ተሸከርካሪዎችንና እቃዎችን በ 10 ቀናት ውስጥ ባይረከቡ ለጨረታ ተሳትፎ ያስያዙት ገንዘብ ለኩባንያው ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል::
 6. ተሸከርካሪዎች በጨረታ እስከተሸጡበት ጊዜ ድረስ የሚፈለግ ግብርና ታክስ ቢኖር የሻጭ ኃላፊነት ይሆናል:: ተሸከርካሪዎቹ ከተሸጡ በኋላ የሚፈለግ ግብርና ታክስ፣ ስም ማዛወርያ እንዲሁም ሌላ ክፍያ ቢኖር የገዢው ኃላፊነት ይሆናል::
 7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ለዚሁ በተዘጋጀ ቅፅ መሰረት የሚገዙትን ዕቃ ዋጋና 15% የተጨማሪ እሴት ታክስን በግልጽ ሁኔታ በተናጥል ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
 8. ከቀረጥ ነፃ ተሸከርካሪዎችን ኩባንያው ለገዢዎች የሚያስረክበው ገዢዎች በቅድሚያ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የሚወስነውን ቀረጥና ታክስ ክፍያ ከፍለው ተገቢውን ማስረጃ ሲያቀርቡ ብቻ ይሆናል::
 9. አሸናፊ ተጫራቾች ተሸከርካሪዎቹንም ሆነ ሌሎች ዕቃዎችን ከሪከቨሪ በራሳቸው ወጪ ሳይነጣጥሉ በጠቅላላ በአንድ ጊዜ ማንሳት ይኖርባቸዋል::
 • ጨረታው ቅዳሜ ሰኔ 05 ቀን 2013 ዓ.ም ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኩባንያው ዋና መ/ቤት ይከፈታል፡፡ ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

 ለበለጠ መረጃ 0115 – 15 45 07፣ 0115 – 51 08 17 ፣ 0115 – 53 53 00፣ 0913 57 01 55 ደውለው መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

Send me an email when this category has been updated