ዘመን ባንክ አ.ማ. አዲስ ላስገነባው ባለ 32 ወለል ህንፃ ለሰራተኞች ካፍቴሪያ እና ሬስቶራንት አገልግሎት በዘርፉ ተሰማርተው አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ ድርጅቶችን አወዳድሮ በውድድሩ ብቁ ከሚሆን ድርጅት ጋር ለ2 (ሁለት) አመት በሚቆይ የውል ስምምነት መስጠት ይፈልጋል፡፡

Zemen-Bank-S.C.-logo-reportertenders-1

Overview

 • Category : Catering Service
 • Posted Date : 01/16/2023
 • Phone Number : 0115575825
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 02/04/2023

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ

     የጨረታ ቁጥር: ZB/28/2023

ዘመን ባንክ አ.ማ. አዲስ ላስገነባው ባለ 32 ወለል ህንፃ ለሰራተኞች ካፍቴሪያ እና ሬስቶራንት አገልግሎት በዘርፉ ተሰማርተው አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ ድርጅቶችን አወዳድሮ በውድድሩ ብቁ ከሚሆን ድርጅት ጋር ለ2 (ሁለት) አመት በሚቆይ የውል ስምምነት መስጠት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መካፈል የምትችሉ መሆኑን ይገልፃል፡፡

 1. በዘርፉ የተሰማሩ እና የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ /TIN/ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
 2. ተጫራቾች የጨረታውን የቴክኒካል እና የፋይናንሻል ሰነዶቻቸውን ኦሪጂናል እና ኮፒ ለየብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 200,000.00 (ብር ሁለት መቶ ሺህ) በCPO ወይም ሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከመክፈቻው ሰዓት በፊት ከቴክኒክ መጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸው፡፡
 4. የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 00 (ብር ሁለት መቶ) በሂሳብ ቁጥር 1031710004707010 በማንኛውም የዘመን ባንክ ቅርንጫፍ በመክፈል ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡30 እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከ 7፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡00 ሰዓት ከባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት 15 ፎቅ የግዥና ውል አስተዳደር መምሪያ ቀርበው መውሰድ ይችላሉ፡፡
 5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥር 26 ቀን 2015 ዓ.ም በ300 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ በ315 ሰንጋተራ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ንግድ ስራ ት/ቤት ፊት ለፊት15 ፎቅ የግዥና ውል አስተዳደር መምሪያ ይከፈታል፡፡
 6. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 ለተጨማሪ መረጃ፡-

አድራሻ፡– ሰንጋተራ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የንግድ ሥራ ት/ቤት ፊት ለፊት 15 ፎቅ

የግዥና ውል አስተዳደር መምሪያ፣ ስልክ ቁጥር 0115575825/0115574052

ዘመን ባንክ አ.ማ

Ras Abebe Aragaye St.  P.O. Box 1212     Tel. +251115573525/+251115575825/+251115574052 Addis Ababa, Ethiopia