ዘመን ባንክ አ.ማ የመጋዘን ሕንጻ እድሳት ጨረታ ማስታወቂያ

Zemen-Bank-S.C.-logo-1

Overview

  • Category : House & Building Construction
  • Posted Date : 01/11/2021
  • Phone Number : 0115575825
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 01/30/2021

Description

የመጋዘን ሕንጻ እድሳት ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ZB/21/2021

ዘመን ባንክ አ.ማ ለመጋዘን አገልግሎት ለመጠቀም የገዛውን ህንጻ ለማስጠገንና እድሳት ለማስደረግ በደረጃ-4 ግንባታ ዘርፍ ላይ ልምድ ያላቸውን እና ከዚያ በላይ የሆኑትን የሥራ ተቋራጮችን በጨረታ በማወዳደር ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ከግንዛቤ በመውሰድና ሥራዎቹን በአካል በቦታው ተገኝታችሁ በመመልከት የስራውን ዝርዝር ዋጋና ስራውን ሰርቶ በማጠናቀቅ ለማስረከብ የሚፈጅባችሁን ጊዜ ገልጻችሁ የቴክኒክና የዋጋ መወዳደሪያ ሃሳባችሁን በሁለት የተለያዩ ኤንቨሎፖች እንድታቀርቡ በጨረታው የተጋበዛችሁ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከቴክኒክ መወዳደሪያ ሰነዳችሁ ጋር አያይዛችሁ የምታቀርቧቸው ሰነዶች

1.1. በባንኩ ዋና ቅርንጫፍ በመቅረብ በአካውንት ቁጥር 1031710004707010 ብር አንድ መቶ (100.00) በመክፈልና የጨረታ ሰነዱን ከፋሲሊቲ ማኔጅመንት መምሪያ በመውሰድና ቅፆችን ሞልቶ በመምሪያው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት፡፡

1.2. የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ ኮፒ፤

1.3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት ኮፒ፤

1.4. የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬትና መለያ ቁጥር (Tin No) ሰነድ ኮፒ፤

1.5. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ) (CPO) ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሰነድ ማቅረብ፤

2. የጨረታ ሰነድ አቀራረብ

2.1. ከላይ ከአንድ እስከ አምስት የተዘረዘሩትን ሰነዶች ከቴክኒክ ሰነዶች ጋር በአንድ ኤንቨሎፕ ውስጥ ከትቶ በማሸግ ከኤንቨሎፑ ፊት ለፊት የቴክኒክ መወዳደሪያ የሚል ጉልህ ፅሁፍ በማኖር ማቅረብ፤

2.2. የፋይናንስ መወዳደሪያ የያዙ ሰነዶቻቸውን በሌላ ሁለተኛ ኤንቨሎፕ በማሸግ ኤንቨሎፑ ፊት ለፊት የፋናንስ መወዳደሪያ የሚል ጉልህ ፅሁፍ በማኖር ማቅረብ፤

3. የጨረታ ማቅረቢያ ጊዜና አከፋፈት ስነስርአት፤

3.1. የጨረታ ማስታወቂያ ለመጀመሪያ ጊዜ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ማለትም ከጥር 17 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በሚቆጠር 16 ተከታታይ ቀናት ማለትም የካቲት 3 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ 3፡30 ሰዓት ድረስ ፋሲሊቲ ማኔጅመንት መምሪያ ተጫራቾች በአካል በመቅረብ የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን እንዲያስገቡ ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ ይቆያል በመሆኑም  የዋጋና የቴክኒክ ሃሳብ የያዙ ኤንቨሎፖችን ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤

3.2. ጨረታው የካተት 3 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ላይ ሳጥኑ ይዘጋል በዚያው ዕለት ከጠዋቱ በ 3፡31 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ተከፍቶ የተጫራቾች የቴክኒክ መወዳደሪያ ሃሳብ የያዙ ኤንቨሎፖች ብቻ ተከፍተው ሰነዶቹ በንባብ ይሰማሉ፡፡

3.3. የተጫራቾች የቴክኒክ ሰነድ ተገምግሞ መስፈርቱን ያለፉና ያላለፉ ተጫራቾች ውጤትና የዋጋ መወዳደሪያ ሃሳብ የያዙ ኤንቨሎፖች መክፈቻ ጊዜን በደብዳቤ ለተጫራቾች ከተገለፀ በኋላ የጨረታ ዋጋ መክፈቻ ስነስርአት ዕለት በቴክኒክ ያለፉ ተጫራቾች ብቻ ፋይናንስ ኤንቨሎፕ ይከፈታል፤

3.4 ባንኩ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን 0115-57-58-25/0115-57-35-25 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

   አድራሻችን ፡ ካዛንቺስ ዘመን ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ፋሲሊቲ ማኔጅመንት መምሪያ በሚገኝበት ገነት ህንጻ 2ተኛ ፎቅ ላይ ነው፡፡

ዘመን ባንክ አ.ማ

Joseph Tito St.  P.O.Box 1212  Tel0115-57-58-25/0115-57-35-25 Addis Ababa, Ethiopia

                                                                      Local Knowledge – International Standards

Send me an email when this category has been updated