ዘመን ባንክ አ.ማ የወጡበት ዋጋ  (par value) ብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር) የሆኑ  ቁጥራቸው 1, 473 የሚደርሱ  የባንኩን  አክሲዎኖች ከሥር በተዘረዘሩት ደንቦች መሰረት በጨረታ የሚሸጥ ይፈልጋል፡

Zemen-Bank-S.C.-logo-reportertenders-1

Overview

 • Category : Bank Related
 • Posted Date : 09/18/2021
 • Phone Number : 0116686215
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 10/04/2021

Description

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር FIS/01/2016 መሠረት   አክሲዎኖችን በጨረታ ለመሸጥ የወጣ ማስታወቂያ

ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ ቁጥር  FIS/01/2016   መሰረት የውጭ ዜግነት ያላቸው በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆኑ ሰዎች በኢትዮጵያ ባንኮች ውስጥ የያዟቸው አክሲዎኖች የባለቤትነት መብት እንዲተላለፍ ተደንግጓል፡፡ በዚህ መመረያ መሰረት ዘመን ባንክ አ.ማ   የወጡበት ዋጋ  (par value) ብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር) የሆኑ  ቁጥራቸው 1, 473 የሚደርሱ  የባንኩን  አክሲዎኖች ከሥር በተዘረዘሩት ደንቦች መሰረት በጨረታ የሚሸጥ በመሆኑ ፍላጎት ያላቸው እና በህግ ክልከላ የሌለባቸው ግለሰቦች  ወይም ተቋማት  የሚከተሉትን ደንቦች በመከተል በጨረታው  ላይ እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡-

 1. ተጫራቾች ለዋጋ ማቅረቢያ የተዘጋጀ ሠነድ ከዘመን ባንክ አ.ማ ፋይናንስ መምሪያ በመቅረብ መውሰድ እና ሰነዱን ሞልተው በተ.ቁ 2 እና 3 ላይ ከተጠቀሱት ሰነዶች ጋር በማድረግ በፖስታ አሽገው ለዚሁ ዐላማ የተዘጋጀ ፋይናንስ መመምሪያ ውስጥ በሚገኝ የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 2. ተጫራቾች ለመግዛት የሚፈልጉትን የአክስዮን ብዛት በብር 1000 ( አንድ ሺህ ብር) አባዝተው የተገኘውን ውጤት 25% በባንኩ ሥም CPO አሰርተው በተ.ቁ 1 ላይ በተጠቀሰው ፖስታ ውስጥ አድርገው የጨረታ ሣጥኑ ውስጥ  ማስገባት አለባቸው፡፡
 3. ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ወይም በትውልድ ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን የሚያሳይና ግለሰብ ከሆኑ መታወቂያ ፣ፓስፖርት መንጃ ፍቃድ በውክልና ከሆነ የተወካይ እና ወካይ መታወቂያ፣ፓስፖርት ወይም መንጃ ፍቃድ እና የውክልና ሰነድ ኮፒ በተ.ቁ 1 ላይ ከተጠቀሰው ሰነድ ጋር አያይዘው የጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት አለባቸው ፡፡ተጫራቹ ተቋም ወይም ድርጅት ከሆነ ድርጅቱን ወክሎ የሚሣተፈው ሰው መታወቂያ ፣ድርጅቱን እንዲወክል ሥልጣን የተሰጠበት በአግባቡ የተመዘገበ ሰነድ ፣የድርጅቱ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ኮፒ በተ.ቁ 1 ላይ ከተጠቀሰው ሰነድ ጋር አብረው ተያይዘው ሣጥኑ ውስጥ ማስገባት አለባቸው ፡፡
 4. የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ እና ሌሎች ሰነዶች (ከላይ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱት ) ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስከ መስከረም 24 ቀን 2014ዓ.ም 11፡00ሠዐት ድረስ የጨረታ ሣጥኑ ውስጥ ማስገባት ይቻላል፡፡
 5. ጨረታው በመስከረም 25 ቀን 2014ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ተወካዮቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
 6. ጨረታው የሚከፈተው ካዛንችስ በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት 8ኛ ፎቅ ላይ ነው፡፡
 7. ተሳታፊዎች ያሸነፉበትን ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃለው ለባንኩ ማስገባት አለባቸው:: ይህን ካለደረጉ ባንኩ ተጫራቹ ያስያዘውን CPO የሚወርስ ይሆናል፡፡አክስዮኖቹንም እንደገና ለጨረታ ያቀርባል፡፡
 8. ባንኩ ሐራጁን የመሰረዝ ሙሉ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 9. ተጨማሪ ደንቦችን በተ.ቁ 1 ላይ በተጠቀሰው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ተቀምጠዋል፡፡
 10. ለተጨማሪ መረጃ በሚከተሉት የስልክ ቁጥሮች ደውለው ማነጋገር ይችላሉ፡- 011 6 68 62 15 ወይም 011 6 68 62 16 ወይም 011-5-54 00 43 ወይም የባንኩ ፋይናንስ ወይም ህግ ክፍል በአካል በመቅረብ ተጨማሪ ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

               ዘመን ባንክ አ.ማ

                Joseph Tito St.  P.O.Box 1212        Tel: 011-554 00 53

 Addis Ababa, Ethiopia

                     Local-Knowledge International Standards