ዘመን ኢንሹራንስ አ.ማ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ለዋና መስሪያ ቤት አገልግሎት የሚውል ህንጻ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Zemen-Insurance-Share-Company-logo-1

Overview

  • Category : House & Building Purchase
  • Posted Date : 10/24/2022
  • Phone Number : 0116151125
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 11/09/2022

Description

ዘመን ኢንሹራንስ አ.ማ

   የህንጻ ግዢ ጨረታ ማስታወቂያ

ዘመን ኢንሹራንስ አ.ማ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ለዋና መስሪያ ቤት አገልግሎት የሚውል ህንጻ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ማንኛውም መስፈርቱን የምታሟሉ ህንጻ ያላችሁና መሸጥ የምትፈልጉ ህጋዊ የባለቤትነት ማረጋገጫ ያለችሁ የህንጻ ባለይዞታዎች ከዚህ በታች በተገለጸው ዝርዝር መስፈርት መሰረት እንድትወዳድሩ ተጋብዛችኋል፡፡

የሚፈለገው ህንጻ ዝርዝር መስፈርቶች

ተ.ቁ ዝርዝር መግለጫ ተፈላጊ መስፈርት
1 የቦታው ጠቅላላ ስፋት ከ 300 ካ.ሜ ያላነሰ
2 የህንጻው ወለል ስፋትና ከፍታ ከ G+5 ያላነሰ

–         ምድር ቤት (Basement) ያለው ቢሆን ይመረጣል

3 የመኪና ማቆሚያ ቦታ መኪና ማቆሚያ ያለው
4 ህንፃው የሚፈለግበት አካባቢ ከመሐል ከተማ እሰከ የሚከተሉት አካባቢዎች ድረስ ፡

ልደታ፣ ሳር ቤት፣ ቄራ፣ ጎፋ፣ ጎተራ፣ ሳሪስ፣ ቦሌ ዙሪያ፣ 24 አካባቢ፣ 22 አካባቢ፣ካሳንቺስ፣ አራት ኪሎ፣ ፒያሳ፣ ጥቁር አንበሳ ጀርባ፣ ጌጃ ሰፈር

5 የባለቤትነት ማረጋገጫ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ፣ከማንኛውም የባንክ እና ሌላ እዳና እገዳ ነጻ የሆነ፣በቀላሉ ስም ማዛወር የሚችልና ምንም አይነት የህግ ክርክር የሌለበት
6 ተፈላጊ ዶክመንት የተሟላ የባለቤትነት ካርታና የዘመኑ ግብር የተከፈለበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
7 ህንጻው የሚገኝበት ልዩ ቦታ በዋና አስፓልት ፊት ለፊት ወይም ከ 200 ሜትር በላይ ገባ ያላለ/ በግልጽ ሊታይ የሚችል
8 ህንጻው ያለበት ሁኔታ ህንጻው የስትራክቸር ፣የጣራ፣የወለል ንጣፍ እና ሌሎች ጉድለቶች የሌሉበት
9 ከንግድ ደንበኞች ጋር ያለው ቀረቤታ የተሻለ የንግድ እንቅስቃሴ ያለበት አካባቢተመራጭ ይሆናል
10 አሳንሰርና የአደጋ ጊዜ መውጫ ህንፃው ቢያንስ አንድ ሊፍት እና የአደጋ ጊዜ መውጫ ደረጃዎች ያሉት ቢሆን ይመረጣል
11 የኤሌክትሪክ ሀይል አገልግሎት ዋናው የኤሌክትሪክ ሀይል መስመር በሚቋረጥበት ወቅት ተለዋጭ በቂ ሀያል ጄነሬተር ያለው ቢሆን ይመረጣል
12 የውሃ አቅርቦት በህንጻው ምድርና ጣራ ላይ በቂ የውሃ ማጠራቀሚያ ያለው ቢሆን ይመረጣል
13 የእሳት አደጋ መከላከያ ተንቀሳቃሽ የእሳት ማጥፍያና ህንጻው ላይ የተገጠመ በውሃ የሚሰራ የእሳት ማጥፊያ (Fire Hydrant) የተገጠመለት ያለው ቢሆን ይመረጣል
14 የኮሚኒኬሽን አገልግሎት የስልክ፣የኢንተርኔትና የዳታ መስመር ዝርጋታ ያለው
15 የሳኒተሪ አገልግሎት በእያንዳንዱ የህንጻ ክፍል በቂ የሆነ የመጸዳጃ ክፍሎችና እና የእጅ መታጠቢያዎች ያሉት
  1. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 15 የስራ ቀናት ውስጥ ቦሌ በሚገኘው አለም ህንጻ ዘመን ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት 2ኛ ፎቅ ለዚሁ በተዘጋቸው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይቻላል
  2. ተጫራቾች በተጠቀሰው አድራሻ ለጨረታ ማስገቢያ የተዘጋጀውን ቅጽ ዘወትር በስራ ሰዓት ያለምን ክፍያ ከሰው ሀብትና ንብረት አስተዳደር መምሪያ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ያስገቡት የጨረታ ሰነድ ጥቅምት 30 ቀን 2022 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው እለት ከጠዋቱ 5 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ጨረታው በሚከፈትበት ቀንና ሰዓት መገኘት ይችላሉ
  4. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ዘመን ኢንሹራንስ አ.ማ ዓለም ሕንጻ ሁለተኛ ፎቅ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0116-15-11-25 ደውለው ማግኘት ይችላሉ፤