የሀበሻ ቢራ አክስዮን ማህበር በዘርፉ የተሰማሩ ከደረጃ 1 እስከ 4 የሆኑ የሀገር ውስጥ የትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢ ድርጅቶችን በጨረታ በማወዳደር ከአሸናፊው ድርጅት/ቶች ጋር እንደ ሁኔታው የሚታደስ ለ1 (አንድ) ዓመት የድርጅቱን ምርቶች የማጓጓዝ የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ መፈራረም ይፈልጋል።
Overview
- Category : Transport Service
- Posted Date : 01/11/2023
- Phone Number : 0984059671
- Source : Reporter
- Closing Date : 01/23/2023
Description
ሐበሻ ቢራ አክስዮን ማህበር
የትራንፖርት አገልግሎት ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የሀበሻ ቢራ አክስዮን ማህበር በዘርፉ የተሰማሩ ከደረጃ 1 እስከ 4 የሆኑ የሀገር ውስጥ የትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢ ድርጅቶችን በጨረታ በማወዳደር ከአሸናፊው ድርጅት/ቶች ጋር እንደ ሁኔታው የሚታደስ ለ1 (አንድ) ዓመት የድርጅቱን ምርቶች የማጓጓዝ የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ መፈራረም ይፈልጋል።
በመሆኑም ተጫራቾች፡-
- በዘርፉ የተሰማሩ መሆናቸውን የሚገልፅ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ሰርተፍኬት፣ የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን የጭነት አገልግሎት የደረጃ ብቃት ማረጋገጫ የምዝገባ ፈቃድ ሰርተፍኬት የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ለድርጅቱ በቋሚነት የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ቢያንስ 20 /ሃያ/ ባለ ተሳቢ ኢቪኮ (IVECO) ማቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የፋይናንሻል ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ ፣የቴክኒክ ሰነድ ኦርጅናል በማለት እና የጨረታ ማስከበሪያ በተለያዩ ኢንቨሎፖች በማድረግ አራቱንም ኢንቨሎፖች በአንድ ላይ በማሸግ ከዚህ በታች በተጠቀሰው የማህበሩ አድራሻ ” የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ ጨረታ” የሚል በመጻፍ የመጫረቻ ሰነዳቸውን ጥር 15 ቀን 2015 ዓ/ም ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ወይም ቀደም ብሎ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 10,000 (አስር ሺህ ) በሲፒኦ ብቻ ሐበሻ ቢራ አክስዮን ማህበር ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የትራንስፖርት አገልግሎት ዋጋ በሙሉ ጭነት (40 ቶን) በኪሎ ሜትር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ጥር 15 ቀን 2015 ዓ/ም ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዳቸውን በፖስታ በማሸግ በተጠቀሱት ቀናት በስራ ሰዓት ግዥ ዋና ክፍል ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
- ሁሉም መኪኖች ጂ.ፒ.ኤስ. ያላቸው አና ለድርጅቱ የጂ.ፒ.ኤስ መግቢያ ወይም አካሰሰ የመስጠት ግዴታ አለባቸው፡፡
8.ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡ ሐበሻ ቢራ ፋብሪካ አክስዮን ማህበር ጽ/ቤት
ካርጎ ፊት ለፊት አዲሰ የልብ ህክምና ሆስፒታል ጎን
ስ.ቁ 0984059671/0913153994
አዲስ አበባ፣
ኢትዮጵያ