የላፍቶ ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት በህጋዊ ይዞታው ላይ የሚገኘውን 2400 ካሬ ሜት ቦታ በጨረታ ለማከራየት ይፈልጋል፡፡

Overview

  • Category : House & Building Rent
  • Posted Date : 09/29/2022
  • Phone Number : 0114190105
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 10/07/2022

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የላፍቶ ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት በህጋዊ ይዞታው ላይ የሚገኘውን 2400 ካሬ ሜት ቦታ በጨረታ ለማከራየት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህም ቦታውን ባለበት ሁኔታ ተከራይቶ መገልገል የሚፈልግ ማንኛውም ተወዳዳሪ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቦታውን በአካል በመመልከት የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ከደብሩ የዕለት ገንዘብ ተቀባይ የማይመለስ 500 ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የሚከራዩበትን ዋጋ በካሬ ሜትር በመጥቀስ እንዲሁም ለምን አገልግሎት እንደሚከራዩት ጭምር በተዘጋጀው ሰነድ ላይ በመሙላት የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት እስከ 10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በደብሩ ጽ/ቤት ለጨረታው በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ በታሸገ ፖስታ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን የጨረታ ሳጥን በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች እንዲሁም የደብሩ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አባላት ፤ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ፤ የን/ላፍቶ ክ/ከ ቤተክህነት ተወካዮች እንዲሁም የሚመለከታቸው የጽ/ቤት ሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ይከፈታል። ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 0114 19 01 05 ፤ 091156547፤ 0912023863  ደውሎ ማነጋገር ይቻላል።

ማስታወሻ ደብሩ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡