የሐበሻ ሲሚንቶ አክሲዮን ማህበር የዳይሬክተሮች ቦርድ 11 ኛውን የባለአክሲዮኖች መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ

Habesha-Cement-logo

Overview

 • Category : Announcement
 • Posted Date : 06/04/2021
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 06/26/2021

Description

ለሐበሻ ሲሚንቶ አክሲዮን ማህበር ባለአክሲዮኖች በሙሉ

የስብሰባ ጥሪ

የሐበሻ ሲሚንቶ አክሲዮን ማህበር የዳይሬክተሮች ቦርድ 11 ኛውን የባለአክሲዮኖች መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ በሰኔ 19 ቀን 2013 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ ለማካሄድ እንደሚከተለው ጥሪውን ያቀርባል፡፡

የስብሰባው አጀንዳ

 1. እ.ኤ.አ የ2020 ሂሳብ ዓመት ዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርት መስማት
 2. እ.ኤ.አ በዴሴምበር 30,2020 የተጠናቀቀውን የሒሳብ ዓመት የውጪ ኦዲተሮች ሪፖርት መስማት
 3. በሁለቱ ሪፖርቶች ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ
 4. በጎደሉ ሁለት የዳይሬክተሮች ቦርድ መቀመጫዎች ምትክ ለመተካት ተወያይቶ መወሰን
 5. የእለቱን ቃለ ጉባዔ ማጽደቅ

ማሳሰቢያ

 • በዕለቱ በስብሰባው ላይ መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ኢትዮቻይና ወዳጅነት ጎዳና፣ ከወሎ ሠፈር ወደ ጎተራ በሚወስደው መንገድ ወንጌላዊት ህንጻ ፊት ለፊት ካስማ ህንጻ ፣ 8ኛ ፎቅ በሚገኘው የሐበሻ ሲሚንቶ ዋና መስሪያ ቤት ስብሰባው ከሚካሄድበት ከሶስት ቀናት በፊት በአካል በመቅረብ የውክልና ፎርም በመሙላት ወክልና መስጠት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
 • ሕጋዊ ወኪሎች ያሏቸው ባለአክሲዮኖች ወኪሎቻቸው በሠነዶች ምዝገባ የተረጋገጠ ውክልናቸውን በመያዝ በስብሰባው ላይ መገኘት ይችላሉ፡፡
 • በስበሰባው እለት ባለአክሲዮኖችም ሆኑ ወኪሎቻቸው ባለአክሲዮን መሆናቸውን የሚያሳይ ሠነድ፣ የአክሲዮን ሰርተፍኬት እና መታወቂያ ይዘው መምጣት ይኖርባቸዋል፡፡

የሐበሻ ሲሚንቶ አክሲዮን  ማህበር የዳይሬክተሮች ቦርድ