የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በስሩ ለሚገኙ ሰራተኞች የሥራ ላይ ደህንነት መጠበቂያ እና የአደጋ መከላከል አልባሳቶች ግዥ አስመልክቶ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Purchases
- Posted Date : 09/04/2021
- E-mail : info@dce-et.com
- Phone Number : 0114403434
- Source : Reporter
- Closing Date : 09/23/2021
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- DCE/OI/99/2021
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በስሩ ለሚገኙ ሰራተኞች የሥራ ላይ ደህንነት መጠበቂያ እና የአደጋ መከላከል አልባሳቶች ግዥ አስመልክቶ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡-
- ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፣ ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የታደሰ ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡት ገንዘብ በተጫራቾች መመሪያ 7.3 እና 7.4 በተጠቀሰው መሠረት መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሠነዱ በተጠቀሰው ብዛት እና ስፔሲፊከሽን መሠረት መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ወሎ ሰፈር አካባቢ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዋና መ/ቤት የግዥ የሥራ ሂደት ኬዝ ቲም ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸው በሚያቀርቡበት ወቀት ለሚጫረቱባቸው አልባሳቶች አብሮ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ መስከረም 13/2014 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው መስከረም 13/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ 4፡15 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡– የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0114-40-34-34
ማዞሪያ 0114-42-22-70/71/72
E-MALL አድራሻ info@dce-et.com
የድህረ ገፅ አድራሻ WWW.dce-et.com
ፖሳ.ቁ 3414 ፋክስ ቁ. 0114-40-04-71/0114-42-07-46
ወሎ ሰፈር የቀድሞው ኖሬላ ግቢ