የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለመከላከያ ዋና መ/ቤት ህንፃ ግንባታ ለተካተተው አዲስ የውስጥ ለውስጥ መንገድ እና ተያያዥ ስራዎች አገልግሎት የሚውል የአሸዋ እና ጠጠር ምርትና አቅርቦት ግዥ ለመፈፀም በጨረታ ሰነዱ ላይ በቀረበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Defence-Construction-Enterprise-14

Overview

 • Category : Construction Raw Materials
 • Posted Date : 09/21/2021
 • Phone Number : 0118493823
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 10/08/2021

Description

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር DCE ፕሮ/11-10B/47/2012

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለመከላከያ ዋና መ/ቤት ህንፃ ግንባታ ለተካተተው አዲስ የውስጥ ለውስጥ መንገድ እና ተያያዥ ስራዎች አገልግሎት የሚውል የአሸዋ እና ጠጠር ምርትና አቅርቦት ግዥ ለመፈፀም በጨረታ ሰነዱ ላይ በቀረበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም፡-

 1. ተጫራቾች በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
 2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስረከቢያ ዋስትና የሚያቀርቡት ገንዘብ በተጫራቾች መመሪያ ተራ ቁጥር 7.3 እና 7.4 በተጠቀሰው መሰረት መሆን አለበት
 3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ/ በመክፈል ቅዳሜን ጨምሮ ፕሮጀክቱ በሚገኝበት ጦር ሀይሎች ፊት ለፊት በምድር ሀይል ግቢ ውስጥ ባለው ቢሮአችን ድረስ በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
 4. የጨረታ አሽናፊው ወደ ስራው ሲገቡ የውለታው 10% የመልካም ስራ አፈፃፀም ማስያዝ ይጠበቅባቸኋል፡፡
 5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ መስከረም 28 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰአት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 6. ጨረታው መስከረም 28 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፕሮጀክቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
 7. አሸዋ እና ጠጠሩን ፕሮጀክት ሳይት ድረስ በራሱ ትራንስፖርት ማቅረብን ያጠቃልላል፡፡
 8. ፕሮጀክቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻጦር ኃይሎች ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው ምድር ኃይል ግቢ ውስጥ በሚሰራው ህንፃ ፕሮጀክት መምጣት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ለበለጠ መረጃ:- uስልክ ቁጥር 0118-49 38 23