የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለድሬዳዋ ምስራቅ ዕዝ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል Supply install, Test of elevator አቅርቦትና ገጠማ ግዥ ሥራን አስመልክቶ በንዑስ ተቋራጭ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Machinery
- Posted Date : 09/25/2021
- E-mail : INFO@dce-et.com
- Phone Number : 0114403434
- Source : Reporter
- Closing Date : 11/02/2021
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCE/SF/105/2021
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለድሬዳዋ ምስራቅ ዕዝ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል Supply install, Test of elevator አቅርቦትና ገጠማ ግዥ ሥራን አስመልክቶ በንዑስ ተቋራጭ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡-
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ፣ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በተጫራቾች መመሪያ ተራ ቁጥር 7.3 እና 7.4 በተጠቀሰው መሠረት መሆን አለበት፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ካታሎግ፣ የታደሰ የሦስተኛ ወገን የጥራት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት (Renewed 3rd Party Quality Certification ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ወይም ጨረታው በሚከፈትበት ሰዓት በካታሎጉ ላይ የሚወዳደሩበትን ዕቃ ለይቶ በማመልከት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ወሎ ሠፈር አካባቢ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዋና መ/ቤት የግዥ የሥራ ሂደት ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ዕቃዎች በተጠቀሰው ብዛት (Quantity) መሠረት መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ጥቅምት 22/2014 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ጥቅምት 22/2014 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡– የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0114-40-34-34
ማዞሪያ 0114-42-22-70/71/72
ፖ.ሳ.ቁ 3414 ፋክስ ቁ. 0114-40-04-71/0114-42-07-46
ወሎ ሰፈር የቀድሞው ኖሬላ ግቢ
ድህረ ገፅ፡- WWW.dce.gov.com/www.dce.et.com
ኢሜል:INFO@dce-et.com