የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለፕሮጀክቱ አገልግሎት የሚሰጥ በጥሩ ይዞታ ላይ የሚገኙ ከ12 ሠው በላይ የሚይዙ ሁለት ተሽከርካሪዎችን ከነአሽከርካሪያቸው ጭምር በጨረታ አወዳድሮ ላልተወሰነ ጊዜ መከራየት ይፈልጋል፡፡

Defence-Construction-Enterprise-2

Overview

 • Category : Vehicle Rent
 • Posted Date : 10/09/2022
 • Phone Number : 0911691378
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 10/17/2022

Description

    ኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሚኒስቴር

      ከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ   

         F.D.R.E Ministry of Defense                ቁጥር/Ref.No. Pro/18-02B/4479/15

Defense Construction Enterprise         ቀን/Date 24 /01/2015E.C      

በድጋሚ የወጣተሽከርካሪ ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ

     የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በቆሬ አካባቢ እየገነባ ለሚገኘው የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ግንባታ ፕሮጀክት (18-02B) ለፕሮጀክቱ ሰራተኞች ሰርቪስ እና ቀን እንደአስፈላጊነቱ ለፕሮጀክቱ አገልግሎት የሚሰጥ በጥሩ ይዞታ ላይ የሚገኙ ከ12 ሠው በላይ የሚይዙ ሁለት ተሽከርካሪዎችን ከነአሽከርካሪያቸው ጭምር በጨረታ አወዳድሮ ላልተወሰነ ጊዜ መከራየት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ባለንብረቶች ወይም ህጋዊ ውክልና ያላቸው ተወካዮቻቸው የተሽከርካሪውን ነዳጅ በተከራዩ የሚሸፈን መሆኑን በመገንዘብ በታሸገ ፖስታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቅዳሜን ጨምሮ ባሉት 7 (ሰባት) ተከታታይ የሥራ ቀናት በቆሬ አደባባይ በሚገኘው የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ማዕከል የፕሮጀክት አቅርቦት እና ግዥ ቡድን ቢሮ በግንባር በመቅረብ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን በማሟላት ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ፡-

 • የተሽከርካሪ ኪራይ ዋጋ በቀን ________________
 • ተሽከርካሪው በሊትር የሚጓዝበትን ኪሎ ሜትር ______________
 • የተሽከርካሪው ስሪት እ.ኤ.አ ከ1996 ወዲህ ቢሆን ይመረጣል፡፡
 • የተሽከርካሪዎች መነሻ (ማደሪያ) ቦታ______________
 • የሰርቪስ መነሻ ቦታዎች ቱሉ ዲምቱ አደባባይ እና መገናኛ አደባባይ ናቸው፡፡

መያያዝ ያለባቸው ሠነዶች

 • የምዝገባ ሰርተፍኬት
 • የታደሰ የንግድ ፈቃድ
 • ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል
 • የግብር ከፋይ (Tin) ኮፒ የታደሰ
 • ጨረታው በሰባተኛው ቀን በፕሮጀክት ቢሮ ከቀኑ በ8፡00 ሠዓት ተዘግቶ በ8፡15 ሠዓት የሚከፈት ሲሆን 7ኛው ቀን እሁድ ወይም በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡
 • ከተሽከርካሪው ማደሪያ ቦታ እስከ ሰርቪስ መነሻ ቦታ ድረስ ያለው ርቀት (የነዳጅ ፍጆታ) ለተሽከርካሪው ከተሰጠው ዋጋ ጋር ተደምሮ ይሰላል፡፡
 • ድርጅቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

     ለበለጠ መረጃ፡- ለበለጠ መረጃ 0911-69-13-78/ ወይም 011-8-72-03-83

በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርሰፕራይዝ የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ፕሮጀክት (18-02B)