የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የጃንሜዳ ስታፍ ኮሌጅ (11-09B) እና (20-03B) ህንፃ ፕሮጀክት ስራ አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፡፡
Overview
- Category : Construction Machinery & Equipment
- Posted Date : 01/16/2023
- Phone Number : 0118959810
- Source : Reporter
- Closing Date : 02/01/2023
Description
የጨረታ ማስታወቂያ፡-
የጨረታ ቁጥር DCE/Pk/018/2015
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የጃንሜዳ ስታፍ ኮሌጅ (11-09B) እና (20-03B) ህንፃ ፕሮጀክት ስራ አገልግሎት የሚውል፡-
- Floor standing central main distribution board
- Surface Mounted main distribution board
- Flush mounted sub distribution board ብዛታቸውና ስፔስፊኬሽናቸው በጨረታ ሰነድ ውስጥ በሚገለፀው መሠረት ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡-
1 ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደሰ ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
2 ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡት ገንዘብ በተጫራቾች መመሪያ ተራ ቁጥር 7.3 እና 7.4 በተጠቀሰው መሠረት መሆን አለበት፡፡
3 ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰአት ቅዳሜን ጨምሮ ተከታታይ 13 የስራ ቀናት ጃንሜዳ ስታፍ ኮሌጅ (17-06B) ፕሮጀክት የስታፍ ኮሌጅ ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኘው የፕሮጀክት ገንዘብ ያዥ ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
4 ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ካታሎግ ፣ ሦስተኛ ወገን የምርት ጥራት ማረጋገጫ (Product Quality Certificate) በጨረታው ቴክኒካል ሰነድ ማካተትና ካታሎግ ላይ የሚወዳደሩበትን ዕቃ ለይቶ በማመልከት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
5 ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ጥር 23/2015 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
7 ጨረታው ጥር 23/2015 ዓ/ም ከቀኑ 8፡30 ከሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፕሮጀክቱ ቢሮ ይከፈታል፡፡
8 ፕሮጀክቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
የጃንሜዳ አዣዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ፕሮጀክት (17-06B)
የቀጥታ ስልክ ቁጥር ዐ118-95-98-10 ወይም 0118121352