የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የሰላም ማስከበር ማእከል ህንፃ ግንባታ ፕሮጀክት (20-03B) ስራ የሚውል፤ Sanitary Material and Fixtures ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Construction Machinery & Equipment
- Posted Date : 01/25/2023
- Phone Number : 0118121352
- Source : Reporter
- Closing Date : 02/11/2023
Description
የጨረታ ማስታወቂያ፡-
የጨረታ ቁጥር DCE/JA.PEC.KE/0018/2015
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የሰላም ማስከበር ማእከል ህንፃ ግንባታ ፕሮጀክት (20-03B) ስራ የሚውል፤
Lot1. Sanitary Material and Fixtures
ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡
1 ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
2 ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡት ገንዘብ በተጫራቾች መመሪያ ተራ ቁጥር 7.3 እና 7.4 በተጠቀሰው መሠረት መሆን አለበት፡፡
3 ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰአት ቅዳሜን ጨምሮ ተከታታይ 15 ቀናት ጃንሜዳ ስታፍ ኮሌጅ (17-06B) ፕሮጀክት የስታፍ ኮሌጅ ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኘው የፕሮጀክት ገንዘብ ያዥ ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
4 ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ካታሎግ ፣ ናሙናና የጥራት ማረጋገጫ (Quality Certificate) ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ወይም በጨረታ መክፈቻ ቀን በካታሎጉ ላይ የሚወዳደሩበትን ዕቃ ለይቶ በማመልከት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
5 ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ዕቃዎች የ3ኛ ወገን(Authorization) እና ቴክኒካል ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
6 ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ የካቲት 03/2015 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
7 ጨረታው የካቲት 03/2015 ዓ/ም ከቀኑ 8፡30 ከሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፕሮጀክቱ ቢሮ ይከፈታል፡፡
8 ፕሮጀክቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
የጃንሜዳ አዣዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ፕሮጀክት (17-06B)
የቀጥታ ስልክ ቁጥር ዐ118-95-98-10 ወይም 0118121352