የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የጃንሜዳ ስታፍ ኮሌጅ ፕሮጀክት ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሠረት 01 (አንድ) ቶዮታ ኮረላ ስሪታቸው 2001 እና ከዛ በላይ የሆነ መኪና ለፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ ሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጥ መከራየት ይፈልጋል፡፡

Defence-Construction-Enterprise-5

Overview

 • Category : Vehicle Rent
 • Posted Date : 01/25/2023
 • Phone Number : 0118959810
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 02/04/2023

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረ ቁጥር DCE/JN,PK/017/2015

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የጃንሜዳ ስታፍ ኮሌጅ ፕሮጀክት ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሠረት 01 (አንድ) ቶዮታ ኮረላ ስሪታቸው 2001 እና ከዛ በላይ የሆነ መኪና ለፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ ሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጥ መከራየት ይፈልጋል፡፡

ተፈላጊ መስፈርት

 1. ተጫራቾች በጨረታው ወቅት በዘርፉ የንግድ ፈቃድ የባለቤትነት የምስክር ወረቀት የኢንሹራንስ ሽፋን እና ተዛማጅነት ያላቸውን ሠነዶች ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 2. ተጫራቾች ያቀረቡት መኪና በብልሽትም ሆነ የተለያዩ ችግሮች ሲገጥማቸው አገልግሎቱ እንዳይቋረጥ ተክቶ ሊሠራ የሚችል መኪና ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
 3. ተጫራቾች ያቀረቡት መኪና በሊትር ስንት ኪሎሜትር እንደሚጓዝ በጨረታ ሰነድ መግለፅ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
 4. ተከራይ የነዳጅ ወጪውን በራሱ የሚሸፍን ሆኖ ተጫራች(አከራይ) መነሻው ደብረዘይት መድረሻው አዲሰ አበባ የሆነ መኪና ከነሹፌሩ አገልግሎት ለመስጠት በቀን የሚያስከፍሉትን ዋጋ ብቻ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ዋጋው የመንገድ ፈንድ በፈጣን መንገድ ለመጓጓዝ የሚጠይቀውን /ዕለታዊ ክፍያን ያካተተ መሆን አለበት፡፡
 5. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ሰባት (7) ተከታታይ የስራ ቀናቶች ቅዳሜን ጨምሮ በግንባር በመቅረብ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 24/05/2015ዓ/ም በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በ8፡30 በፕሮጀክቱ ቢሮ ይከፈታል፡፡
 6. ፕሮጀክቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ

የጃንሜዳ አዣዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ፕሮጀክት (17-06B)

የቀጥታ ስልክ ቁጥር ዐ118-95-98-10 ወይም 0118-12-13-52

6 ኪሎ(ወደ ፈረንሳይ ቤላ መንገድ መሄጃ)የሚገኘው የመከላከያ አዣዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ካንፕ ውስጥ